”አሁንም ዘላቂ መፍትሄ የሚመጣው በሰላምና ድርድር መሆኑን እናምናለን፣ ከተገፋን ግን ለህልውናችን ስንል እርምጃ እንደምንወስድ ይታወቅልን!”

(ከትግራይ ሰራዊት ወታደራዊ ኮማንድ የተሰጠ መግለጫ)

ጠላት የጀመረውን የማጥቅት ዘመቻ አሁንም ያለውን ሁሉ አቅም ተጠቅሞ ሰፊ ርብርብ እያደረገ ይገኛል። የመከላከል መስመራችን ለመስበርና በዛ አድርጎም ትግራይና የትግራይ ህዝብን ለማበሳበስ የሚችለው ሁሉ እያደረገ ቢሆንም እንኳን ማድረግ አልተቻለውም።

የትግራይ ህዝብ ኩራትና አለኝታ የሆንከው ጀግናው ሰራዊት ጠላት የከፈተብህን የማጥቃት ዘመቻ በላቀ ፅናት መክተህ ምሽግህ ሳታስደፍር እያካሄድከው ያለኸው ተአምራዊ ገድል ታሪካዊ ነው። ከፊትህ ያለው ሀይል ያ ትናንት የምታውቀውና ደጋግመህ ያሸነፍከው ሀይል ነው። ሰላምን ገፍቶ የጀመረው ጥቃት መክተህ ለላቀ ተልእኮ ተዘጋጅ።

ጠላት ላለፉት 5 ወራት የሰላም ሀይል መስሎ አለምን ለማደናገር እና እየተውተረተረ ቆይቷል። ለጦርነት ያስፈልጋል ያለው ሁሉም አይነት ዝግጅት እያደረገ ከቆየ ብኋላ በሀይል ህልሙ እና ፍላጎቱ ለማሳካት ሲል በደቡብ ትግራይ ግንባር ወረራ ጀምሯል። በምዕራብ ግምባርም ጥቃት ለመጀመር ዝግጅት እያደረገ እንዳለ በጥብቅ እየተከታተልነው ነን።

ጠላት ላለፉት ጥቂት ወራት ግጭት ቆሞ ወደ ሙሉ የሰላም እና ድርድር ለመግባት ሲደረግ የቆየውን ጥረት ጨርሶ እንዲዘጋ እያደረገ ይገኛል።

ይህ ፀረ ህዝብ የሆነውን ስርዓት የሰላምን መንገድ ተጠይፎ በውስጡ ያለውን ሁሉን አቀፍ ቀውስ እና አለመረጋጋት በጦርነት ለመሸፈን ብሎ ወደ ከፋ እልቂት እና ጥፋት የሚያስገባ ተግባር እየፈፀመ ይገኛል።

ከጦርነት እና ቀውስ ውጪ መኖር የማይችለው ይህ ፀረ ህዝብ ሀይል የትግራይ ህዝብ ለማጥፋት ብቻ ሳይሆን በመላው ኢትዮጵያ መብቴ፣ ሰላም፣ ልማት፣ ዴሞክራሲ ያለና የጠየቀ ህዝብ እየጨፈጨፈ በየቀኑ የንፁሃንን ህይወት በከንቱ እንዲረግፍ እያደረገ ይገኛል። በኦሮምያ፣ዓፋር፣ ሶማሌ ፣ ቤንሻንጉል፣ ጋምቤላ፣ደቡብ ክልል እና በአማራ ህዝብ ላይ ማለቅያ የሌለው ግፍና እልቂት እየፈፀመ ይገኛል። ሁሉም ሊገነዘበው የሚገባው ነገር ጠላት ባህሪው ይህ ነው። እያደረገው ያለውም ይህ ነው።

የትግራይ ህዝብ እና መንግስት ለሰላም እና ድርድር ያላቸው ዝግጁነት ከመግለፅም አልፈው በተግባርም ሊደረግ የሚገባውን ጥረት እያደረጉ ቆይተዋል። ሰላም የተመኘነው በሰላማዊ ሁኔታ ውስጥ ሆነን አይደለም። ለሰላም ብለን በህዝባችን ላይ እየደረሰ ያለውን ሁሉም አይነት መከራ ስቃይ ተሸክመን፣ በረሀብ እና በበሽታ በየቀኑ ህይወት እየገበርን ነው ለሰላም እጃችን ዘርግተን የቆየነው።

ከዛሬ ነገ መፍትሄ ይመጣል ብለን ለመሸከሙ የሚከብድ ሰቆቃ ተሸክመን፣ ልብ ገዝተን ስንጠብቅ ቆይተናል። አሁንም ዘላቂ መፍትሄ የሚመጣው በሰላም እና ድርድር መሆኑ ዛሬም ይሁን ነገ የማይነቃነቅ ፅኑ እምነታችን ነው።

ጠላት የሰላም መንገድ ገፍቶ በጀመረው የሚቀጥል ከሆነ ለህልውናችን እና ዘላቂ ደህንነታችን ስንል እርምጃ ለመውሰድ እየተገደድን እንዳለን አለም አቀፍ ማህበረሰብ እንዲሁም የኢትዮጵያ ህዝቦች ሀይሎች ሊገነዘቡ ይገባል።

ህልውናችንና ደህንነታችን በክንዳችን!!

ትግራይ ትስዕር!!

የትግራይ ሰራዊት ወታደራዊ ኮማንድ

ነሓሴ 18/2014 ዓ/ም

መቐለ