ለምን ይመስለሃል?

ገና ከጥንት ከጥዋቱ ኣንተን በመክዳት ነው የጀመሩት። ፖለቲካቸውም ከውጪ ሃይሎች ጋር ተመሳጥረው ኣንተ ላይ ሴራ በመጎንጎንና ከጀርባ በመውጋት የተቃኘ ነው። ኣንተ ከወራሪ ግብፃውያን ጋር በጉራዕና በጉንደት ኣንገት ለኣንገት ስትተናነቅ እነሱ ግን ከግብፅ መሪው ከዲቭ እስማኤል ጋር ደብዳቤ ሲፃፃፉና ሲመካከሩ የነበሩ ሰዎች ናቸው። 

ለምን ይመስለሀል? 

ኣንተ ዶግዓሊ ላይ ወራሪ ነጮችን ለመጀመርያ ጊዜ ድባቅ ስትመታቸው እነሱ ግን በራስ መኮንን በኩል ከጣልያን ጋር ደብዳቤ ሲፃፃፉ ነበር። “የምንፈልገውን ነፍጥ ከሰጣችሁን ከኛም ጋር ወዳጅነት ከመሰረታችሁ ዶግዓሊ ላይ የፈሰሰው ደማችሁን እኛ እንበቀልላችኃለን” ሲሉ ወራሪ ጣልያናውያንን ሲለማመጡ የነበሩ የከሀዲ ከሀዲ እኮ ናቸው። ይሄም ኣልበቃ ብልዋቸው ነጭ ወራሪ ለመጅመርያ ጊዜ የተሸነፈው ዓድዋ ላይ እንደሆነ ኣስመስለው የውሸት ትርክት በመፍጠር እነሱ ስለሌሉበት ብቻ የዶግዓሊ ድልህን ለማንኳሰስ የተፍጨረጨሩ ድኩማን እኮ ናቸው። እነሱ እኮ ከቅኝ ገዢዎች ጋር ተዋውለው ግዛትህንና ህዝብህን ለሁለት የከፈሉ ናቸው። 

ኣዎ! ኣፄ ዮሃንስ የጎንደር ህዝብንና ቤተ ክርስቲያናትን ከድርቡሽ ወራሪዎች ለመከላከል መተማ ኣንገቱን ሲሰጥ እነሱ ግን ግዛትህንና ህዝብህን እንዴት ለሁለት መክፈል እንደሚችሉ ቀን ከሌት ሲያስቡ ነው የነበሩት። ኣስበውም ኣልቀሩ! መተማ ላይ የፈሰሰው ደሙ እንኳን ገና ሳይደርቅ ሰሜናዊ ግዛትህና ህዝብህን ለጣልያን ለመስጠት የውጫሌ ውልን በጥድፊያ የፈረሙ ነውረኞች እኮ ናቸው። እነሱ እኮ ጣልያናውያንን “ትግሬዎች መሳሪያ እንዳያገኙ የባህር በሮችን ሁሉ ዝጉልን እንጂ በግዛት ኣንጣላም፤ እናንተ የሰሜኑን እኛ ደግሞ የደቡብን ትግሬ እንይዛለን” ብለው ከቅኝ ገዢ ጋር ተስማምተው የገዛ ህዝባቸውና ግዛታችውን እንደ ቅርጫ ስጋ የተቀራመቱ እጅግ ኃላ ቀር ፖለቲከኞች እኮ ናቸው።     

ታዲያ ይሄን ያደረጉት ለምን ይመስለሀል?

እነሱ እኮ ከጣልያን የተረፈ የትግራይ መሬትም ሰፍቶባቸዋል። እህ! ቢሰፋቸውም ኣይደል ግዛትህን ቆርጠው ቆራርጠው ወደ ቤጌምድርና ወደ ወሎ ክፍለ ኣገሮች የወሰዱት? ኣሁን የወልቃይትና የራያ ግዛቶችህን ወረው የያዙት እኮ ያኔ ኣያቶቻቸው ያደረጉትን ነው እየደገሙት ያሉት። ሌላ ምንም ኣዲስ ነገር የለውም።   

እነሱ እኮ “ያፈረሰ ቄስ ኣይቀድስ፣ የሸሸ ንጉስ ዳግመኛ ኣይነግስ” ብለህ እውነቱን ስትነግራቸው፣ የከፋ የኢኮኖሚ፣ የፖለቲካና የማንነት ጭቆና በቃኝ ስትላቸው “ትግሬ ጠግበዋልና ኣይቀጡ ቅጣት ይቀጣ፣ ከዱላ በስተቀርም ምንም ዓይነት ጠመንጃ በእጁ ኣይያዝ” ብለው በመዛት ምህረት ኣልባ ቅጣት ሊቀጡህ እንደ ልማዳቸው ከውጪ ኃይሎች ጋር ህብረት የፈጠሩ የዕድሜ ልክ ከሀዲዎች ናቸው። ኣንተ የእምቢ ኣልገዛም፣ የበቃኝ ባይነት ምልክት የሆነውን የቀዳማዊ ወያነ ኣመፅህን ስታቀጣጥል ልክ ኣሁን እያረጉት እንዳሉት የውጪ ሀይል ጋብዘው የእንግሊዝ የጦር መኮንኖችን ኣስከትለው ዘምተውብሃል። ኣንተም በኣምባ ኣላጀ ላይ ኣይቀጡ ቅጣት ቀጥተህ ኣንድ የእንግሊዝ መኮንንም ገድለህ ልካቸውን ኣሳይተሀቸዋል። እነሱም ከዚህ በኃላ ነበር ከቀዳማዊ ወያነ ጀግኖች ጋር ፊት ለፊት መዋጋት እንደማይችሉ ተረድተው ከእንግሊዝ የጦር ኣውሮፕላኖችና ኣብራሪዎችን ለምነው የትግራይን ህዝብ ያለ ምህረት በገበያ ላይ የጨፈጨፉት። የሰውና የእንስሳት ስጋና ደም እስኪ ቀላቀልም እላይህ ላይ ቦምብ ያዘነቡት። 

ታዲያ ይሄ ለምን ይመስለሀል? ይሄ የዛሬ ክህደታቸውስ እንደ ደራሽ ውሃ ዝም ብሎ ድንገት የመጣ ይመስለሃል እንዴ? ኣይደለም! በፍፁም ኣይደለም! እነሱ ከውጪ ሃይል ጋር ማበር የትናንት፣ የዛሬና የነገም ስልታቸው ነው።

አረ ለምን ይመስለሀል ባንዳነታቸው ኣንተ ላይ ሊያላክኩ፣ ኣገር ሻጭነታቸው በማይረባ ትንታኔ ሊያስደግፉ፣ እጅና እግር ቆራጭነታቸው ያንተ ምክር ሊያስመስሉ፣ የኣገር ክህደታቸው በኣንድነት ስም ሊሸፋፍኑ የሚንደፋደፉት? ጎንደር ውስጥ “የትግሬ ማጮህያ” የሚል ቦታ ሰይመው በዛ ቦታ ላይ “ትግሬ ገዳይ” እያሉ እየፎከሩ ሀሴት የሚያደርጉስ ለምን ይመስለሀል? ጥላሁን ግዛው ለኣዲስ ኣበባ ዪኒቨርሲቲ የተማሪዎች ህብረት ፕረዚደንትነት ሲወዳደር ትግራዋይነቱ እንደ ኃጥያት ተቆጥሮበት “እሱ እኮ ትግሬ ነው” የሚል ዘመቻ የተከፈተበትና እንዳይመረጥ ሲቀሰቀስበት የነበረው ለምን ይመስለሀል? 

ኣባታችን ልኡል ራስ መንገሻ ስዩምን በ14 ዓመታቸው ያለ ወንጀላቸውን ወንጅለው በለጋ እድሜያቸው ጭንቀት እስኪይዛቸው ድረስ ለተከታታይ ሰባት ወራት ጥብቅ ምርመራ ሲያደርጉባቸው ቆይተው በንጉሰ ነገስቱ ዙፋን ችሎት ላይ ምን እንዳልዋቸው ኣታውቅም እንዴ? ልኡል ራስ መንገሻ ራሳቸው “የትውልድ ኣደራ” በሚል መፅሃፋቸው ከገፅ 51 እስከ ገፅ 52 ላይ እኮ ቃል በቃል እንዲህ ነው ያሉት፦ ከንጉሰ ነገስት ችሎት ቀረብኩኝ። ጃንሆይ ዙፋናቸው ላይ እንዳሉ ወንጀሉ ይነበብ ተባለ። ልዑል ጌታዬ ራስ ስዩምም እዚያው ኣጠገባቸው ነበሩ። ልዑል ራስ ካሳ ኃይሉ፣ ልዑል ኣልጋ ወራሽ ኣስፋ ወሰን፣ ልዑል ራስ እምሩ /ስላሴና ሌሎችም መሳፍንትና መኳንንትም ኣብረው ኣሉ። ከእሳቸው ዙፋን በታች ግን ጠቅላይ ሚኒስትሩና ሚኒስትሮቹ ተቀምጠዋል። ሊጋባውም ኣሉ። ሌላው ህዝብ ግን ያኔ በደንብ ኣድርጎ ለኣገሩ ሲከላከል የነበረው ኣርበኛ ሁሉ ግራና ቀኝ ተኮልኩለዋል። በጣም ትልቅ ትዕይንት ነው። ትዕይንቱ ከዚያ በፊት ኣልተደረገም፣ ከዚያ በኃላም የተደረገ ኣይመስለኝም። ይነበብ ተባለና ወንጀሌ ሲነበብ ብዙ ከፍተኛ ወንጀሎች ተዘረዘሩ። እንዴት ኣድርጌ ህዝቡን እያሰባሰብኩ፣ ሰንጋ እያሳረድኩ፣ በምሰጠው ግብርና በምሰራው ሁሉ የማደርገው ኣመራር ከወያኔዎች ጋር መላላክም፣ መግባባትም እንዳደረግሁ። 

ኣይዟችሁበማለትም፣ እሮሮ በማስማትልዑል ጌታዬም እዚያ ታስረዋል እንግዲህ እንደዚህ ያለ ጭቆና ደርሶብናል፣ በጦርነቱም ላደረጋችሁት ውለታ ምንም ዓይነት ወሮታ ኣልተከፈለምእያልኩ ህዝቡን እንደማነሳሳ ነው የተተረከው። በዚህ ዓይነት መንገድ ኣንድ ሰዓት ተኩል ሙሉ የፈጀ የወንጀል ክስ ከቀረበ በኃላ ሰው ሁሉ በጣም ተገረመ። ታሪኩ ሲወራ ስለ ሰነበተና የተደረገው ነገር ሁሉ ከባድ ስለሆነ መዝገቡ እንዳለቀ እኔም እምነት ክህደቴን ሳልጠየቅ ሴራውን ሲያቀነባብሩ የነበሩና በጠቅላላው እንደዚህ ያለ ኣመለካከት ያለው ሁሉ ትግራይ ዘላለም እንዳወከ፣ በመንግስት ላይ እንዳመፀ የሚኖር ህዝብ ነው። በጠላት ጊዜ እንዲህ፣ እንዲህ ኣድርጎ፣ እምባ ኣርዓዶም ላይ ራስ ሙሉጌታን ወግቶ፤ ራያ እንደዚህ ኣድርጎበማለት በትግራይ ላይ ያልተባለ ክፉ ድርጊትና ያልተወንጀለበት ነገር የለም” እኮ ነው ያሉት፤ ራሳቸው ኣባታችን ልኡል ራስ መንገሻ። 

ታዲያ ይሄ ለምን ይመስለሃል?     

አረ ሌላውን ትተህ ኣብይ ኣህመድ የሚያደንቀውና በየጊዜው የሚደጉመው ኢሳት ቴሌቪዥን ግጥሚያው 95 ሚሊዮን ለ 5 ሚሊዮን ነውና የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ ተነስና ከትግራይ የሆነውን ሁሉ ኣጥፋ፣ ዓሳውንም ለመያዝ ባህሩን ኣንጥፍ ብሎ ያወጀው ለምን ይመስለሀል? ሴት ልጅህን ሲደፍሩ ደምሽን እያጠራን ነው፣ ኣማራ እንድትሆኚ ውለታ እየዋልንልሽ ነው እያሉ የሚሳለቁና በቁስልዋ ላይ እንጨት የሚሰዱትስ ለምን ይመስለሀል? እናትህን በኣራት ልጆችዋ ፊት ከደፈሯት በኃላ ሁሉንም ልጆቹን እፊቷ ገድለው ድጋሚ ማህፀንሽ መውለድ የለበትም ብለው ማህፀኗ ላይ ባዕድ ነገር የጨመሩባት ለምን ይመስለሀል? ቅዱሳን ኣባቶችህ ራሳቸው ከመሰረቱትና ከትውልድ ወደ ትውልድ እየተተካኩ ለዘመናት በምንኩስና ከኖሩበት የዋልድባ ገዳም በማንነታቸው ምክንያት ኣባረዋቸው ሲያበቁ ያለ ሃፍረት በምንፍቅና የከሰሱዋቸው ለምን ይመስለሃል? ጦርነቱ ከተጀመረ በኃላ ነው እንዴ መናፍቃን የሆኑት? ለመሆኑ ትምክህተኞቹ ሃይማኖት ከቅዱሳን ኣባቶችህ ተምረው ሲያበቁ መልሰው ኣባቶችህን በምንፍቅና የመክሰስ ሞራልስ ከየት ኣገኙ? 

ፋሺስቱ ኣብይ ኣህመድ ‘ምታ ነጋሪት ክተት ሰራዊት’ ብሎ የዘር ማጥፋት ጦርነት ሲያውጅብህ ትምክህተኞቹ እሰይ እሰይ ስለቴ ሰመረ፣ ስለቴ ስመረ እያሉ እየዘመሩ ከዓይን ጥቅሻ በፈጠነ ሩጫ ኣንተን መውጋት የጀመሩትስ ለምን ይመስለሃል? መቐለ የሶርያው ኣሌፖ ትሆናለች እያሉ ያሟረቱት፣ ሻዕቢያ ገብቷል ሲባሉ እነሱ ኢትዮጵያን ያውቅዋት ይመስል ‘ሃ ሃ ሃ ትግሬዎቹ እኮ ኢትዮጵያን ኣያውቅዋትም’ ያሉት፣ ወንድ የሆነ ትግሬ ሁሉ ጁንታ ነውና ይገደል ያሉት፣ ማይካድራ ላይ በሚዘገንን መንገድ ጨፍጭፈውህ ሲያበቁ መልሰው ጭሆትህን የቀሙህ፣ የትግራይ ህዝብ ተራበ ሲባሉ የኣባታቸው የኣፈወርቅ ገ/የሱስን ተረት ተረት ይዘው ‘ኣንበጣ ይቆርጥም’ ያሉት . . . 

ለምን ይመስለሃል? እኮ ለምን?

እነዚህ የታሪክ ኣተላዎች ‘መላኩ ተፈራ የእግዚሄር ታናሽ ወንድም፣ የዛሬን ማርልኝ ከእንግዲህ ኣልወልድም’ የሚል የምስኪን እናቶቻቸውን ጭሆት ከመቅፅበት ረስተው የሓውዜን ቁስልህ እንዲያመረቅዝ ሳያፍሩ ባደባባይ ‘መንጌ ቆራጡ መሪያችን’ ያሉት፣ ‘ከኣማራ ጋር እንኳን ኣብሮ መኖር ኣብሮ መለመንም ኣይቻልም’ ሲል የነበረው ደም መጣጩ ኢሳያስ ኣፈወርቂን በጎንደርና በኣዲስ ኣበባ እንጥላቸው እስኪ ወድቅ ድረስ ‘ኢሱ ኢሱ’ እያሉ እየጮሁ በቀይ ምንጣፍ የተቀበሉት ለምን ይመስለሃል? 

ኢሳያስ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻቸውን የወርቅ ጥርሳቸውን እንኳን ሳይቀር እያወለቀ እንዳባረራቸው እያወቁ እነሱ ግን ኤርትራውያንን ‘እናንተ ከኢትዮጵያ ስትባረሩ ትግሬዎች ቤቶቻችሁን ወረሱ’ የሚል እጅግ ነውረኛ ፅሁፍ ይዘው ኣደባባይ ለመውጣት ያላፈሩትስ ለምን ይመስለሃል? መቐለ ተያዘች ሲባል የጎንደርና የባህርዳር ኣደባባዮች ደስታ ባሰከራቸው ሰዎች የተጥለቀለቁት፣ ከትግራይ የፈለቁ የኢትዮጵያ እና የትግራይ ነባር ኣመራሮች እነ ኣቦይ ስብሓትን ጨምሮ ተያዙ ሲባሉ በደስታ ሌሊቱን ሙሉ ሲትኩሱ ያደሩት እኮ እነዚህ ትምክህተኞች ናቸው።     

ቆይ! ቆይ! ረሃብን እንደ ጦር መሳሪያ መጠቀምስ ቢሆን ከኣባታቸው መንግስቱ ኃ/ማሪያም ኣይደለም እንዴ የተማሩት? ምን ኣዲስ ነገር ኣለው! በ1977 ዓ.ም በጦር ሜዳ ያጡትን ድል ኣንተን በረሃብ በመፍጀት ኣይደል እንዴ ያካካሱት? ታዲያ ይሄ ለምን ይመስለሀል?     

አረ ለመሆኑ ለምን ይመስለሀል ከትናንት እስከ ዛሬ የሂትለርና የሞሶሎኒ ጭካኔን በሚያስንቅ ድርጊታቸው ነውር እየፈፀሙብህ ያሉት? ላንተ ያላቸው ጥላቻ ኣይደለምን? በእውነቱ! መቅኔያቸው ድረስ ዘልቆ የገባ መርዘኛ ጥላቻቸው ኣይደለምን? 

ኣዎ! ዛሬ እቅጩን እነግርሃለሁ። ኣንተ ወይ ኣልመሰለህም ወይም ኣንድ ቀን ወደ ልቦናቸው ይመለሱ ይሆናል ብለህ ነው እንጂ እነሱ ኣምርረው ከጠሉህ ዘመናት ተቆጥረዋል። ኣዎ! ትምክህተኞቹ ኣንተን ካልጠሉ በእምነታቸው የማይፀድቁ፣ በፖለቲካቸውም መምራት የማይችሉ የሚመስላቸው እጅግ ግብዞች ናቸው። ኣዎ! ኣንተ የተሻሻልክ፣ ተቀባይነት ያገኘህም ሲመስላቸው ዓይናቸው የሚቀላ፣ በድንጋይም ወግረው ሊገድሉህ የሚቸኩሉ መንፈሰ ቃኤል የተጠናወታቸው ምቀኞች ናቸው። ከኣንድ ሚሊዮን በላይ ህዝብህ ከምዕራብ ትግራይ ኣፅድተው፣ ግዛትህንም በወረራ ይዘው ሲያበቁ ኣሁን ተመልሰው “የሰሜን ኢትዮጵያ ህዝብ መጣላት የለበትም፣ የኣማራና የትግራይ ህዝቦች ደም መቃባት የለባቸውም” እያሉ የሚሳለቁ ነውረኞች ናቸው። ፈረንጆች እንዲህ ዓይነት ሰዎችን ሂፖክራቶች ይሉዋቸዋል፤ ግብዞች እንደ ማለት ነው። አረ ለመሆኑ ምንስ ቀራቸው? ወይስ ኣባታቸው ጎቤ መልኬ እንዳለው ስድስት ሚሊዮን ተጋሩን ስላልገደሉ ደም የተቃቡ ኣልመሰላቸውም?

ወዳጄ! ጥላቻቸው በህወሓት ምክንያት የመጣ ከመሰለህ ኣንተ በእውነቱ እጅግ የዋህ ሰው ነህ። እነሱንም በፍፁም ኣታውቃቸውም ማለት ነው። የምመክርህም ትንሽ የታሪክ መፅሃፍትን ገለጥ ገለጥ እንድታደርግ ብቻ ነው። የህወሓት ሰራዊት 1983 ዓ.ም ገና እግሩ ኣዲስ ኣበባ እንደረገጠ ያ ኣፈ-ቀላጢያቸው ታማኝ በየነ ምን እንዳለ ዪቲብ ገብተህ እየውና ኣንተ ላይ ያላቸው ጥላቻ ሥር የሰደደ መሆኑን ትረዳለህ። የትምክህት የፕሪንት ሚዲያዎች “ትግራይ እስክትለማ፣ ሌላው ኣገር ይድማ” እያሉ መርዝ መርጨት የጀመሩት እኮ ገና ኣዲሱ መንግስት ኣገሪቷን የማረጋጋት እንጂ የልማት ስራዎች እንኳን በቅጡ ባልጀመረበት ጊዜ ነው። በ1997 ዓ.ም ከምርጫ በፊት “ወደ መጡበት እንመልሳቸዋለን” ሲሉህ ከምርጫ በኃላ ደግሞ “ትግሬ ወደ መቀሌ፣ ዕቃ ወደ ቀበሌ” ያሉህ እኮ ስለሚጠሉህ እንጂ ስለሚወዱህ ኣይደለም። 

ወዳጄ! ነጋድራስ ገ/ሂወት ባይከዳኝ “ኣፄ ምኒሊክ የትግራይን ህዝብ እንደራሳቸው ህዝብ ኣላዩትም” ሲሉህ እኮ ዝም ብለው ሳይሆን ትምክህተኞቹ ኣንተ ላይ የነበራቸውና ያላቸው ጥላቻ ምን ያህል ሥር የሰደደ እንደሆነ ተጨባጭ ማስረጃ ነው። ከፈለግክ ደግሞ የእውቁ ባንዳው ኣፈወርቅ ገ/የሱስን መፅሃፍ ኣንብብና እነዚህ ሰዎች ምን ያህል ባንተ ጥላቻ እንደናወዙ ይገባሃል። የትግራይ ልጃ-ገረዶች በ10 እና በ20 ወታደሮች እየተደፈሩ፣ ህፃናት በጥይት እየተቆሉ፣ እናትህ ደም እምባ እያነባች ባለችበት ጊዜ ያ ዲያቆን ተብየው ዳንኤል ክብረት “ኣሁን ኢትዮጵያ ከፍታ ላይ ነች፣ ከዚህ ከፍታም መውረድ የለባትም” ሲል እኮ ጥላቻውን ነው በግልፅ ያንፀባረቀው።              

ሰሞኑን ደግሞ በቅዱስ ፓትርያርኩ ላይ በተነሳው ውዝግብ ምክንያት የተወሰኑ ትምክህተኞች ብፁእ ወ ቅዱስ ኣቡነ ማትያስን ደግፈው በመቆማቸው ምክንያት ኣንተን የደገፉና ትልቅ ውለታ የዋሉልህ መስለው እያወሩ ነው። እነዚህ ደንቆሮዎች ናቸው። ትምክህተኞቹ ኣባታችንን ደገፉ ኣልደገፉ ይሄ የነሱ ጉዳይ እንጂ ያንተ ጉዳይ ኣይደለም። ኣባታችን እንደሆኑ የሚያምኑበትን ተናግረው ግዴታቸውን ተውጥተዋል። የትግራይ ህዝብም የፈለገው ይሄን ነበር። ኣባታችን እውነት በመናገራቸው የሚመጣባቸው ማንኛውም ነገር ካለም በፀጋ እንደሚቀበሉ ጥርጥር የለውም። ከዛ ውጪ ግን በትግራይ ህዝብ ላይ የህልውና ኣደጋ የጋረጠው የትምክህተኞቹ የጥላቻ ፖለቲካ ሆኖ ሳለ የሁሉም ኦርቶዶክሳውያን ኣባት የሆኑትን ፓትርያርክ ስለደገፉ ኃጥያታቸው ከቶ ሊሰረይላቸው ኣይችልም። ኣይገባምም። 

ከዚህ ኣኳያ የኢትዮ 360 ሚዲያ ጋዜጠኞች እስስታዊ ባህሪ ኣንድ ማሳያ ነው። ለምሳሌ የዛ ሚዲያ ጋዜጠኛ የሆነው ሃብታሙ ኣያሌውን ብንወስድ “ከህወሓት ሰማይ ስር” በሚል መፅሃፉ እስስትነቱና ድንቁርናውን ያሳየበት ሀሳብ ገፅ 44 ላይ እንዲህ ብሎ ፅፏል “ተፈጥሮ ፊቷን ኣዙራ ኣፈር ነስታ የድንጋይ ኮረት የሸለመችውን ኣብዛኛውን የትግራይ መሬት የሚታገለውን ድሃ ገበሬ መርጦ ስለተወለደበት እንዳልሆነ ግን መግባባት ላይ ሊደረስበት ይገባል 

እዚህ ላይ ልጁ ለትግራይ ህዝብ ሀዘኔታ የተሰማው በማስመሰል ነው መርዙን እየረጨ ያለው። ነገር ግን የልጁ ኣገላለፅ በትግርኛ “ኮሓሎ’ያ መሲለንስ መንቆሮ” ወይም በግርድፍ ትርጉሙ “ኳዮች መስለው ዓይን ኣጥፊዎች” እንደማለት ነው።  የፅሁፍ ፊደል ቀርፆ ለኣያቶቹ ያስተማረ የትግራይ ህዝብ ሊታፈር እንጂ ሊታዘንለት ባልተገባ። ልጁም የድንጋይ ዘመን ኣስተሳሰብ የተጠናወተው ሆኖ ነው እንጂ በዚህ የእውቀት ኢኮኖሚ (Knowledge Economy) ዘመን የድንጋይ ኮረትም ቢልዮን ዶላሮች የሚታፈስበት ትልቅ ሃብት ነው። ውለታ ቢስም ቢሆን ነው እንጂ ኣሁን እሱ የሚኮራባቸው ኣብዛኞቹ የታሪክ፣ የስልጣኔና የሉዓላዊነት መገለጫዎች ምንጫቸውና ባለቤታቸው ትግራይና የትግራይ ህዝብ ነው። ግን ውስጡ ያለው ኣያቶቹ በምቀኝነት የጋቱት የትግራይ ጥላቻ ስለሆነ ያዘነ መስሎ “ከድንጋያሟ ትግራይ” መወለድህ እርግማን እንደሆነ ኣስመስሎ ቢሞነጫጭር ኣያስገርምም።               

ለመሆኑ ኣሁን እየተካሄደብህ ያለው የዘር ማጥፋት ጦርነት ዋናው ኣስተባባሪና ኣስፈፃሚ ማን ሆነና ነው! በዚህ ጦርነት ግንባር ቀደም ተሰላፊዎቹ ትምክህተኞቹ ኣይደሉምን? ኣብዪ ኣህመድ እኮ ያደረገው ኣንድ ነገር ብቻ ነው። ይሄም እነሱ ኣንተ ላይ ያላቸው የከረፋ ጥላቻቸውን ነው በደንብ ኣድርጎ የተጠቀመበት። መጀመርያ ለ27 ዓመታት በተቃዋሚ ጎራ ሆነው በዲያስፖራና በኣገር ውስጥ ኣንተ ላይ ሲነዙት የነበረውን መርዘኛ ጥላቻ ወደ ቤተ መንግስት ይዞት ገባና በመንግስታዊ ሚዲያዎች ቀጠለበት፤ መዋቅራዊም ኣደረገው። በመቀጠልም ጦርነቱ ሲታወጅ ተነስና መሬትህን ኣስመልስ ብሎ ኣጋግሎ በነበራቸው ጥላቻ ላይ ቤንዚን ጨመረበት፤ እንደ ፈረስም ጋለባቸው። ማቆሚያ የሌለው የሽምጥ ግልቢያ!   

በቃ! ይሄው ነው። No more, No less! ዳንሰኛው ባጫስ ቢሆን የኣማራ ምሊሻ ጀግና ነው . . . ምንትሴ ምንትሴ ሲል ኣለቃው የቀየሰውን የነሱን ጥላቻ ኣሟጦ የመጠቀም ስልት እየደገመ እንጂ ሌላ ኣይደለም እኮ። ከዛማ ትምክህተኞቹ የኣብይን ተልእኮ ተሸክመው ከሻዕብያም ጋር ተባብረው በጦርነቱና በፕሮፖጋንዳው ዋና ኣስተባባሪዎችና ተዋናዮች ሆኖው መጡ። ኣሁንም ድረስ በውጪና በሃገር ውስጥ ሽንጣቸውን ገትረው የሚከራከሩለትና ግፋ በለው የሚሉት ኣብይ ኣህመድ ወክየዋለሁኝ ከሚለው የኦሮሞ ወገን የመጡ ልሂቃን ሳይሆኑ እነዚህ ትምክህተኞች ናቸው። ለመሆኑ ከሦስት ዓመት በፊት ጀምሮ ከሻዕብያ ጋር ተባብረህም ቢሆን ትግራይን ስበር ሲሉት የነበሩት በኢሳት ቴሌቪዥን የመሸጉ የትምክህት ሃይሉ ጋዜጠኞች  ኣይደሉም እንዴ?  

ትምክህተኞቹ በትግራይ ጥላቻ ስለታወሩ ብቻ የኣብይ ኣህመድና የኢሳያስ ኣፈወርቂ መጠቀሚያ ሆነው ይሄው እስከ ኣሁኗ ደቂቃ ድረስ ከፀሃይ በታች ኣለ የሚባለውን ነውር ሁሉ በትግራይ ህዝብ ላይ እየፈፀሙ ይገኛሉ። ሱዳን እስከ 80 ኪ.ሜ ድረስ ወደ ውስጥ ዘልቃ መሬታቸውን ይዛ እንኳን እነሱ በትግራይ መሬት መወረር ነው ሀሴት የሚያደርጉት። ለ25 ዓመታት መለስ ዜናዊ መሬታችንን ለሱዳን ሰጠብን፣ ኣባይ ፀሃየ በመሬታችን ተፈራረመብን እያሉ ሲያላዝኑ የነበሩት ለምን እንደሆነ ኣሁን ገባህ ኣይደለ? ተጋሩ ከሱዳን ጋር ተዋግተው ያስከበሩላቸውን ድንበር ኣሁን ኣብይ ኣህመድ ሱዳኖችን ጠርቶ ሲሰጥባቸው ምነው ዝም ጭጭ ኣሉሳ? የነዚህን ሰዎች የውቅያኖስን ያህል ጥልቅ ጥላቻ ኣሁን በደንብ ተገለጠልህ ኣይደል? ነውራቸውንስ ኣስተዋልከው ኣይደል? 

ኣዎ! እነሱ ባንተ ጥላቻ ኣቅላቸውን ስተዋል፣ ምንም ነገር ከማድረግም ኣይመለሱም። ምክንያቱም ጥላቻ በጊዜ ካልታከሙት ከራስ ማግኘት ይልቅ በሌሎች ማጣት፣ ከራስ ጤንነት ይልቅ በሌሎች መታመም፣ ከራስ መደሰት ይልቅ በሌሎች ማዘን እንድትደሰት የሚያደርግ ክፉ ደዌ ነው።      

ለዛሬ ኣበቃሁኝ፣ በቀጣይ ጊዜ በሌላ ፅሁፍ እስከንገናኝ ቸር ሰንብቱ!

ትግላችን ኣጭርና መራራ ነው!
ትግራይ ታሸንፋለች!

One thought on “ለምን ይመስለሃል?

Comments are closed.