የዶ/ር ቀጀላ የስርቆት፣ የተዛባና የተፈበረከ የታሪክ ሓቲት መነሻ ምክንያቶች

(በ ተስፋ ኪሮስ)

የዶ/ር ቀጀላ መርዳሳ የተፈበረከና የተመነተፈ ትርክት የ360ቱ ሃብታሙ አያሌውን በተዛባና በተፈበረከ ትርክት ሊያርመው ሲሞክር ከድጡ ወደ ማጡ ኣደረጉት። የባህል ሚኒስትር ሆነው ምን ኣይነት ባህል እንደሚገነቡ ኣስቡት እንግዲህ። ጭራሽ የ7ኛ ክፍለ ዘመን ኣል ነጃሽ (ንጉስ ማለት/ማእረግ እንጂ ስም ኣይደለም)፣ በ14ኛ ክፍለ ዘመን የተጀመረው ባህረ ነጋሲ (ነጋሽ) የገዢ ማእረግ ጋር ኣገናኑት።

የታሪክ ስርቆቱና ፍብረካው ዶ/ር ቀጀላ መርዳሳ የጀመሩት ሳይሆን ቀደም ብሎ በኣህኣዴግ ዘመነ ኣገዛዝ ጀምሮ የኦሮሚያ ክልል መንግስት መማሪያ መፅሓፍ ኣስፅፎ የኦሮሚያ ክልል ተማሪዎች ሲታነፁበት ቆይተዋል። የሌሎች ህዝቦች ታሪክና ትርክት ሲማሩ እውነተኛውን የኦሮሞ ህዝብ ታሪክ ሳይማሩ ይቀሩና ታሪክ ኣልባ እንዳይሆኑ ብቻ ሳይሆን ያልነበረን ልዩነት በማስፋት መቃቃርን እንዳይመግቡ ያሰጋል። የተዛባ፣ የተፈበረከና የተኮረጀ (የተሰረቀ) ታሪክ ውሸቱ ሲገለጥላቸው ምን ያህል ግራ መጋባት (shock) ሊፈጥርባቸው እንደሚችል መገመት ኣይከብድምና።

በታሪኩ የማይኮራና በሌሎች ህዝቦች ታሪክ የሚጓጓ (ከዛም ለመላበስ የሚሻ) ትውልድ ከመቅረፅ ይልቅ፣ የተደረሰበትን ትክክለኛ የኦሮሞ ህዝብ ታሪክ በኩራት ማስተማር እና ገና ያልተጠናውና ያልተገለጠው ቀጣይ ጥናት በማድረግ መሰነዱ የተሻለ መንገድ ይሆን ነበር። ግን ይህንን መንገድ የመረጡት አይመስልም።

የዚህ የስርቆት፣ የተዛባና የተፈበረከ ትርክት መነሻው እንደሚከተለው ይመስለኛል።

ሀ) የኦሮሞ ጎሳዎች በ16ኛው ክፍለ ዘመን ከመዳወላቡ (ደቡብ ምስራቅ ባሌ) ተነስተው ወደ ምስራቅ፣ ምእራብና ማእከላዊ ጦብያ በሚንቀሳቀሱበት ወቅት መንገዳቸው ላይ የሚጠብቃቸው ነባር ህዝብ እርጥብ ሳርና ነጭ ጨርቅ ይዞ ከተቀበላቸው ሳይገድሉ፣ የጎሳቸው ኣካል ያደርጉታል። ”ኦሮሞ ኣቃፊ ነው” የሚባለው ሳይገድል ነባር ማንነት ኣጥፍቶ ኦሮሞ ስለሚያደርግ ነው። እና እርጥብ ሳር ይዘው ተቀብለው ከሞት የተረፉት ህዝቦች ውስጥ በወለጋ ያጋጠመ ክስተት ኣለ።

ለ) ነገር ግን ወለጋ የደረሱ የኦሮሞ ጎሳዎች እርጥብ ሳር ይዘው የተቀበሏቸው ጎሳዎች ቋንቋቸው ወደ ኦሮሚኛ ይቀየር እንጂ ጎሳዊ ማንነታቸው ይታወቃል። በዚህ ምክንያት ከዋነኛ የኦሮሞ ጎሳዎች ተለይተው ይታወቃሉ። ከዛ ኣልፎም ”ትክክለኛ ኦሮሞ ኣይደሉም” ተብለው በኦሮሞ ይታማሉ።

ሐ) ታዲያ የእነዚህ ጎሳዎች ምሁራን (ስማቸው ላለመጥቀስ እንጂ የሚታወቁ ኣሉበት፣ ኣፈሩ ገለባ ያድርግላቸውና እነ ዶ/ር ነጋሶም ከዛ ምድብ ናቸው ይባላል)፣ ኣንድ ትርክት ይዘው ብቅ ኣሉ። እኛ ከኦሮሞ የተለየን ሳንሆን የኦሮሞ ህዝብ ከሰሜን ወደ ደቡብ ተገፍቶ ሲሄድ ተቆርጠን የቀረን ነን የሚል ትርክት ፈበረኩ። እና የኦሮሞ ጎሳዎች ከመዳወላቡ ተነስተው ወለጋ ሲደርሱ ”ወላጆቻችን እርጥብ ቄጤማ ይዘው የተቀበሏቸው ወገኖቻችን መጡ” በማለት እንጂ ከመገደል ለመትረፍ (ህይወታቸው ለማትረፍ) ኣይደለም ኣሉ።

መ) ይኸንን ሰፋ ኣድርገው ኦሮሞ መጀመሪያ ከሰሜን ተገፍቶ ወደ ደቡብ ተሰዶ ነው ድጋሚ ከደቡብ ወደ ምስራቅ፣ ምእራብና ማእከል የተንቀሳቀሰው በማለት የተፈበረከ ትርክታቸው መሰረት ለማስያዝ ደግሞ የሰሜን የኩሽ ቋንቋ ቤተሰብ (በተለይ የኣገው ህዝብ) ታሪክ ስርቆት ላይ እና የቦታና የሰው ስሞችን ወደ ኦሮሚኛ ማጠጋጋት (ዶ/ር ጊደና Fake Etymology ያለው ኣይነት) ጀመሩ። የኦሮሞ ህዝብ ወደ ደቡብ ምስራቅ ባሌ (መዳወላቡ) ተገፍቶ ከመሰደዱ በፊት ሰሜን ጦብያ ይኖር ነበር ነው እያሉን ያሉት።

እንግዲህ የባህል ሚኒስትሩ የተፈበረከ፣ የተዛባና የተመነተፈ የትርክት ግንባታ ባህል መነሻው ይኸው ነው።

%d bloggers like this: