የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የተከዳው በማንን ነው?

“እናቴ በልጅነቴ የኢትዮጵያ ሰባተኛ ንጉስ ትሆናለህ ብላኛለች” ብሎ ወደ ፖለቲካዊ ስልጣን የተቆናተጠው የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ፡ እግሩ 4 ኪሎ ቤተ መንግስት ከረገጠችበት ማግስት ጀምሮ ህዝብን ከህዝብ ጋር የማቀራረብ ሰራ ሳይሆን ህዝብን ከህዝብ ጋር የሚያጋጩ ንግግሮች ሲያደርግ ተደምጠዋል።

የአብይ አሕመድ ፖለቲካ መርየት ላይ ያለው ነባራዊ ሁኔታ ያገናዘበ አካሄድ ሳይሆን ንጉስ ከመሆን የሚመነጨው ፍላጎቱ ተንትርሶ ህዝብ እንዲያጨበጭበለት “መደመር” የሚል ፖለቲካ ሳይሆን የሀይማኖት ሰባክያን በሚዘያዘወትሩት ቃላቶችን የታጨቀ አጀንዳ ይዞ በውታፍ ነቃይ ደጋፊዎቹ አመካኝነት የድጋፍ ሰልፍ አስደረገ።

ለአብይ ተብሎ በተጠራው የመስቀል ኣደባባይ ሰልፍ ላይ ቦምብ በመፈንዳቱ በደቂቃዎች ውስጥ ወደ ቴሌቪዥን ቀርቦ “ፈጻሚዎቹ እነ እንትና ናቸው” ብሎ የተወረወረው ቦንብ ማን እንደፈጸመው በሚመለከተው አካል ተጣርቶ ይፋ ከምሆኑ በፊት ወደ 4 ኪሎ ቤተ መንግስት ተጣድፎ በመሄድ “ካሜራ ማን አምጡልኝ” ብሎ የተለመደችውን የክፋት መግለጫው ሰጠ። ብእዛን ቦንብ በተወረወረበት ግዜ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድን ከአደጋው ካሸሹት አጃቢዎቹ ግማሾቹ ያህል በቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ ግዜ በእጀባ ተሰማርተው የነበሩት የትግራይ ብሄር ተወላጆች እንደነበሩ መረጃዎች ይጦቁማሉ።

 በንግግሮቹ መሀል እምብዛም እማይጠነቀቀው አብይ አሕመድ፡ ከዛቺ ቀን ጀምሮ የትግራይ ተወላጆችን ያነጣጠሩ ትግራውያን የሚያሰይጥኑ እንደ “የቀን ጅብ፣ ጸጉረ ልውጥና ሌሎች ቃላቶችን በመጠቀም ደጋፊዎቹ በትግራይ ተወላጆች ጥላቻ እንዲያዳብሩ እና እንዲያጠቅዋቸው አድርገዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የጀመረው የጥላቻ ንግግር በዛ ኣላቆመም፤ ላለፉት ሶስት ኣመታት በሃገሪትዋ ላይ ለተፈጠሩት ጥፋቶች በሙሉ በሚባል መልኩ ህወሃቶች፣ የህወሃት ተላላኪዎች፣ ትግሪኛ ተናጋሪዎች በሚል ኣንድን ህዝብ እና ኣንድን ፖለቲካዊ ድርጅት ብቻ ኢላማ ባደረገ መልኩ ንግግሮችን ሲያደርግ እንደነበር የቅርብ ግዜ ትውስታ ነው።

በተለያየ ግዜ የትግራይ ህዝብ እንዲጠላ፣ ለኢትዮጵያ ስጋት እንደሆነ ተደርጎ ሲገለጽ፣ ጨፍጫፊ ነው ሲባል እና ትግርኛ ተናጋሪዎች በሚል ዶክመንተሪዎች ሲሰሩበት ነበር።  ላለፉት ሶስት ኣመታት ተጋሩ በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች ሲገደሉ፣ ንብረታቸው ሲወድም፣ ሲታሰሩ ልክ ኣይደለም የሚል ኣካል ኣልነበረም። መጀመርያዉኑም ስም ወጥቶላቸው፣ ስጋት ናቸው ተብለው፣ በሃገሪትዋ ላይ ለሚፈጠሩትና ከዚህ በፊት ለተፈጸሙት ጥፋቶች ተጠያቂ ናቸው ተብለው የቀን ጅብ እና ጸጉረ ልውጥ በሚል ቅጽል ስም ህዝቡን እንደ ህዝብ “ዲ ሂውማናይዝ” የማድረግ ስራ ሲሰራ ነበር።

በ2013 ዓ/ም መባቻም ቢሆን መጀመርያ “ፌደራል መንግስቱ ያልደገፈው ምርጫ ኣካሄዳችሁ” ቀጥሎ ደግሞ “ሰሜን እዝ ከጀርባው ተወጋ”  የሀገሪትዋን ሙሉ የመከላከያ ሰራዊት፣ የኤርትራ ጦር፣ የኣማራ ልዩ ሃይልና ሚሊሻ፣ የሶማልያ ወታደሮች እና የዩናይትድ ኣረብ ድሮኖች ኣንድ ላይ ትግራይን ለማጥፋት ተሰለፉ። እንደተባለው ጥቂት የህወሃት ባለስልጣናትን ለመያዝ እና ህግ ለማስከበር ከሆነ ይህን ያህል ሰራዊት እና የጦር መሳርያ ለምን ኣስፈለገ ብሎ የጠየቀ ኣካልም ኣልነበረም። ቀድሞዉኑ የትግራይን ህዝብ እንደ ጠላት እና እንደ ከሃዲ እንዲቆጠር ተደርጓል እና።

የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በእልህ፣ በቁጭት እና በንዴት ትግራይ ላይ እንዲዘምት “ሰሜን እዝ ከጀርባው ተወጋ፣ ህዝቡን ሊጠብቁ የሄዱትን ወታደሮች በዚህ መልኩ ጨፈጨፍዋቸው በማለት የመከላከያ ሰራዊቱ ወደ ጦርነት እንዲገባ ተደረገ።

መከላከያዉን ማን ነው የከዳው?

በንግስና ግዜው በትግራይ ህዝብ ዘንድ ቅብሉነት በማጣቱ ሁሌም ያሰስበው የነበረው አብይ አሕመድ ከኤርትራው ፕረዚደንት ኢሳይያስ አፈወርቂ ጋር በመመካከር ትግራይን የሚያንበረክክበት ቀን ይጠብቅ እንደነበር እና ለዚህ ዓላማው ደግሞ ትግራይን የመክበብ እንቅስቃሴዎች ያደርግ እንደነበር የትግራይ ሰራዊት አዛዦች ከወራት በፊት ባደረጉዋቸው ቃለ መጠይቆች ተናግረው ነበር።

የትግራይ መከላከያ ሰራዊት ኣዛዦች አንዱ ጀነራል ታደሰ ወረደ በቅርቡ በሰጠው ቃለ መጠይቅ “እኛ ሰሜን እዝ ኣላጠቃንም፤ ያደረግነው ራሳችን የመከላከል እርምጃ ነበር የወሰድነው” ሲል የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ እንደሚለው መከላከያን አልወጋንም፤ ጦርነት አልጀመርንም ማለቱ ይታወሳል።

በስነ ምግባራቸው ምክንያት ከዚህ ቀደም ከሰራዊቱ የተሰናበቱት እንደ እነ ባጫ ደበሌ እና አበባው ታደሰ የመሳሰሉት የጦር አዛዦችን ወደ ሰራዊቱ ተመሰልው ሰራዊቱን ያልተደገረውን ነገር እንደተደረገ አስደርገው በመተረክ ሰራዊቱ በትግራይ ህዝብ ቂም ቋጥሮ ህዝቡን እንዲጨፈጨፍ በማድረግ ረገድም ጠቅላይ ሚኒስትር የአንበሳውን ድርሻ ይወስዳል።

የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ወደ ትግራይ ሲዘምት “የምትዋጉት ሃይል የለም፥ ጸጥታ ለማስከበር ነው የምትሄዱት፣ የሉም፣ ተዳክመዋል፣ የነበራቸውን መሳርያ ሙሉ በሙሉ ኣውድመነዋል፣ ኣቅም የላቸዉም” በማለት በሃሰት ሰራዊቱን ወደ ጦርነት ኣስገባው።

ጠቅላይ ሚኒስተሩ ምንም እንኳን ጦርነቱ ከተጀመረ ኣራት ወራትን እስኪያስቆጥር ድረስ የኤርትራ ሰራዊት ትግራይ ውስጥ እንደሌለ ክዶ ቢቆይም ቀስ በቀስ ግን ማመኑ ኣልቀረም። ታድያ የኤርትራ ተራ ወታደሮች የኢትዮጵያ መከላከያ ጀነራሎችን ሳይቀር እንደሚያዙ እና እንደሚያንጓጥጡ መረጃዎች ሲወጡ ነበር። ያ ከኢትዮጵያ ኣልፎ በሌሎች ሃገሮች ሰላም በማስከበር የሚታወቀውና የሚከበረው የኢትዮጱያ መከላከያ ሰራዊት ትግራይ ውስጥ ተራ የኤርትራ ወታደሮች ሲልኩት እና ሲያንቋሽሹት ነበር የሚዉሉት።

የሲኤን ኤንዋ ጋዜጠኛ ንዒማ ትግራይ ውስጥ ፕሮግራም ለመስራት ብሄደችበት ወቅት ” የኢትዮጵያ ወታደሮች እንዳልፍ ቢፈቅዱልኝም ኤርትራውያኑ ግን ከለከሉኝ” ስትል ገልጻ ነበር። የመከላከያ ሰራዊቱ መወሰን በማይችልበት እና ወሳኞቹ የኤርትራ ወታደሮች በሆኑበት የተናቀው እና የተዋረደው ሉኣላዊነቱ ሲደፈር ምንም ማድረግ ያልቻለው የኢትዮጵያ መከላከያ የተከዳው ንጉስ የመሆን አባዜ በተጠናወተው የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ነው።

በኣንድ ወቅት ኣንድ ኤርትራዊ “ፕሬዝደንት ኢሳያስ ኣፍወርቂ ተጋሩን እና ህወሓትን ወያኔ ብሎ እንደሚጠራ እና የተቀረዉን የኢትዮጵያ ህዝብ ደግሞ ኣማራ” እያለ እንደሚጠራው ተናግሮ ነበር። ባለፈው ግዜም ኣቶ ጌታቸው ረዳ በረሃ ሆኖ በሰጠው ቃለ መጠይቅ ‘ሻዓብያ ለኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ምንም ክብር የለዉም። ሻለቃዎች ናቸው ጀነራሎቹን የሚያዙዋቸው ሁሉንም ኢትዮጵያዊ ኣማራ ነው ሚለው ሻዓብያ ውግያ ላይ ደግሞ ከፊት ኣማራዉን ኣስገባው እያለ ጥይት ማብረጃ ያደርጋቸዋል። ኤርትራውያኑ ከኋላ ሆነው ከፊት የሚያሰልፉት የኢትዮጵያን መከላከያ ነው። መከላከያው ከፊትም ከኋላም ነው የሚተኮስበት” ሲል ተደምጠዋል።

ኣምነስቲ ኢንተርናሽናል ባወጣው ሪፖርት ላይም ኣክሱም ላይ በነበረው ጭፍጨፋ ንጹሃንን ሲገድል የነበርዉን የኤርትራ ወታደር ኣንዱ የመከላከያ ኣባል “እባክህ ተው” ሲለው “ዝምበል ኣህያ” ሲል እንደመለሰለት ይገልጻል። ታድያ መከላከያ ሰራዊቱ በውሸት ፕሮፖጋንዳ እና የሚዋጋዉን ሃይል ኣሳንሶ በመግለጽ የትግራይ ጦርነት ላይ ገብቶ የሻዓብያ ወታደሮች ተላላኪ እንዲሆን የፈረደበት፣ ኣንዴ ኣጥፍተናቸዋል፣ ሌላ ግዜ በንፋስ ላይ የተበተነ ዱቄት ነው በማለት የምትሞቱበት ጦርነት ኣይደለም እያለ በውሽት እሳት ውስጥ የከተታቸው ማን ነው? አብይ አሕመድ አይደለምን?

የትግራይ ሰራዊት እየገፋ ሲመጣም ሰራዊቱ ኣልተነገረዉም። ትግራይ ላይ የነበረው ግዚያዊ ኣስተዳደር እና የሚፈልጋቸውን ኣካላት ሲያስወጣ ሳይነገራቸው እዛው ትግራይ ውስጥ የተረሱ የሰራዊቱ ኣባላት እንዳሉ ይገለጻል። ያም ብቻ ሳይሆን በዘመቻ ኣሉላ ኣባ ነጋ በሰተየመው ውግያ ላይ የተማረኩት ክ 8 ሺ በላይ የመከላከያ ሰራዊቱ ኣባላት የኣማራ እክቲቪስቶች የመከላከያ ሰራዊት ኣባላት ኣይደሉም። ጁንታው ልብስ ኣሰፍቶላቸው ነው እያሉ ሲክዷቸው ተሰምቷል። ጠቅላይ ሚኒስትሩም ጀነራሎቹም ስለተማረኩት የመከላከያ ኣባላት ያለው ነገር የለም። እነዚህ ወታደሮች ሲዘምቱ ጀግኖች ሲማረኩ የእኛዎቹ አይደሉም ተብለው በገዛ መርያቸው ተካዱ።

የትግራይ ሰራዊት የተለያዩ የትግራይ ከተሞችን ሲቆጣጠር “ውሸት ነው።” ሲሉ የቆዩት ጄነራሎቹና ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለምን ታድያ በድንገት መቐለን ለቀው ወጡ? እንዴት በኣንዴ ብዙ የትግራይ ከተሞችን ተቆጣጠሩ? ያ ተዳከመ ፣ ተደመሰሰ፣ ንፋስ ላይ የተበተነ ዱቄት ሆነ ሲባል የነበረ ሃይልስ እንዴት ከ 8 ሺ በላይ ወታደሮችን ማረከ?

መልሱ ቀላል ነው። መንግስት ሰራዊቱን እና ህዝቡን ሲዋሽ ነበር። የትግራይ ሰራዊት በየቀኑ ወደ ትግል በሚገቡ የትግራይ ወጣቶች እየተደራጀ ወታደራዊ ኣቅሙን እያጎለበተ ቢመጣም መንግስት ግን ኣሳንሶ ሲገልጻቸውና ተደምስሰዋል ሲላቸው ነበር። ምክንያቱ ደግሞ የመከላከያ ሰራዊቱ ከምን ዓይነት ሃይል ጋር እንደሚፋለም ሳያውቅ በስሜት እንዲገባ ለማድረግ ነው።

እስካሁን ድረስ ከሶማልያ እናቶች በስተቀር “ልጆቻችን የት ገቡ?” ብሎ የጠየቀ የለም። መንግስት የሶማልያ ተወላጆችን ወደ ስልጠና እልካቹሃለው በማለት ኤርትራ ልኮ ካሰለጠናቸው ቡሃላ ወደ ትግራይ ጦርነት እንዳስገባቸው ይታወቃል። የሶማልያ እናቶችም “ለስልጠና ብላችሁ የወሰዳቹሃቸው ልጆቻችን የት ገቡ?” በማለት በ ዋና ከተማዋ ሞቓዲሾ ኣደባባይ

ላይ ሲያለቅሱ ታይተዋል። የኢትዮጵያ እናት ግን ልጆችዋ የት እንደገቡ ምን ላይ እንደወደቁ ኣልጠየቀችም። በተለያየ ምክንያት የወዳጅ ቤተሰቦቻቸውን መርዶ የሰሙ ሰዎች ማህበራዊ ሚድያ ላይ ፎቶ ሲለጥፉ ዛቻና ማስፈራርያ ሲደርስባቸው ነበር።

መንግስት እስካሁኗ ደቂቃ ድረስ ደመሰስን ብቻ እንጂ ምን ያህል የመከላከያ ሰራዊት እንደሞተ እና እንደተማረከ ይፋ ያደረገው ነገር የለም። ኣሁንም በምን ምክንያት መቐለን ለቀው እንደወጡ፣ የተማረከው እና የሞተው የሰራዊቱ ብዛት በመሸፋፈን ወደ ሌላ ጦርነትና እልቂት ለማስገባት ዝግጅቶችን እያደረገ ይገኛል። ኣሁንም ከዚህ በፊት የትግራይ ህዝብ ከህወሃት ነጻ ስላወጣንው የነጻነት ነፋስ እያጣጣመ ነው፣ የትግራይ እናቶች እያለቀሱ ትታችሁን እንዳትወ

ታድያ በውሸት ፕሮፖጋንዳና በጥላቻ ታውሮ ጦርነት ውስጥ ኣንዲገባ፣ ይሚፋለመውን ሃይል ኣቅም እንዳያውቅ ኣጥፍተናቸዋል ደምስሰናቸዋል፣ መሳርያ የሚባል ነገር የላቸውም እያለ በመዋሸት፣ ሰራዊቱን የሻዓብያ ወታደሮች ተላላኪ በማድረግ፣ የተማረኩትን በመካድ እና በጦርነቱ ለሞቱት የሚገባቸውን ክብር ሰጥቶ እውቅና ባለመስጠት ከምንግስት በላይ ሰራዊቱን ማን ከዳው?