የመጨረሻው ምእራፍ መጀመርያ

የትግራይ ህዝብ ራስን የመከላከል ጦርነት በወሳኝነት ወደ መጨረሻው የድል ምእራፍ እየተሸጋገረ እንደሆነ ወዳጅም ጠላትም የተረዳው ይመስለኛል::

ራስን በመከላከልና ኃይሉን በማጥናከር ላይ የነበረው የትግራይ መከላከያ ኃይል (TDF) ሀ ብሎ በጀመረው የአሉላ አባነጋ የማጥቃት ዘመቻ የስበት መሃል የሆነውን የትግራይ ዋና ከተማ መቐለን ነፃ አውጥቶ አለም በትግራይ ሃይሎች ያለውን ግምት አስቀይሮታል::

በትግራይ እናቶች የተሰየመዉ ሌላኛው የማጥቃት ውሎ በደቡብ ትግራይ ወሳኝ የተባለው የቆቦ መስመር በጣጥሶ ከወደ ደቡብ ምስራቅና ምእራብ እየገሰገሰ ይገኛል::

እነዚህ ወታደራዊ ድሎች በበሳል የፖለቲካ አመራርና ወታደራዊ ስትራተጂ የሚመሩ : ዋና አላማቸው ወራሪው የኢትዮጵያ; የኤርትራ እና የተሰፋፊው የአማራ ሃይልና ረዳት የየክልሉ ጀሌዎች ከመላው ትግራይ ጠራርጎ ማውጣት ብቻ ሳይሆን: ዳግም አንሰራርተው እንዳይመለሱ በያሉበት ለመድቆስም ጭምር ነው::
አሁን በሚያስገርም ፍጥነት በአፋር መስመር: በደቡብና በምእራብ ትግራይ እየተካሄደ ያለው የነፃነት ትግል በአዲስ-አበባ መንግስትና በአለም ህብረተሰብ እየፈጠረ ያለው አዲስ ስጋት እንዴት ይስተናገዳል የሚለው ጥያቄ ለማንሳትና የግል አስተያየት ለመሰንዘር ነው።

ትላንትና ሲፎክርና ፎካሪውን ሲያጅብ የነበረው የህብረተሰብ ክፍል ምን እየሆነነው ያለው: ምንስ ሊያጋጥም ይችላል:: እስቲ በመሬት ላይ ያለውን እውነታና እንድምታው እናስቀድም። የኃይል አሰላለፉ ሙሉ በሙሉ ተቀይሯል:. የትግራይ የመከልከያ ሃይል (TDF) የኢትዮጵያ መከላከያ በወሳኝነት አሸንፏል።

የአማራ ተስፋፊ ሃይል በትግራይ መሬት ላይ ያሰፈራቸው: ስማቸው ቀይሮ ለኢንቨስተሮች የቸረቸራቸው የትግራይ ይዞታዎች ይዞ መቆየት ይቅርና በህይወት ለማምለጥም ጊዜው ጨልሞበታል: የኤርትራ ሰራዊት እንኳን እንደነበረው የኢትዮጵያ ሃይል ሊመራ ይቅርና ለራሱ ሽሽቱን ለማሳመር ገሽሽ ብሎ እየተጠባበቀ ነው::
የኢትዮጵያ ህዝብ በአንድ በኩል በአዲስ አበባ የጁቡቲ መስመር ሊቆረጥ ነው ተብሎ ገንዘብ ያለው ሁሉ ራሱናና ልጆቹን ለማሸሸ ሲጨናነቅ : ሎላው ትግራይ ስተወረርና በውስጥና በውጭ ኃይሎች ስትደፈር ያጨበጨበው አሁን ደግሞ አደባባይ ላይ ወጥቶ ከተሸነፈውና ከተማረከው መከላከያ ጎን እንሰለፋለን ሲል ግራ መጋባቱን ይገልፃል:: በኦሮሞ ሃይሎች የትጥቅ ትግሉ እየገፋ: በሌሎች ክልሎች ደግሞ አዳዲስ የትጥቅ ትግል ጀማሪዎች ብቅ ብቅ ማለት ጀምሯል: የ1983 አ.ም. ኢህአዴግ አዲስ አበባን ለመቆጣጠር ሲቃረብ የነበረው ሁኔታ እንዳለ እየተደገመ ነው::

የመንግስቱ ዘመን ሊያበቃ ቀናት ሲቆጠሩ የነበረው ሽርጉድ አሁንም አለ:: የመሪዎች ንግግሮች ሁሉ ከዚያው ዘመን የተቀዱ ይመስላሉ:: መንግስቱ ወደ ዝምባብዌ ሲያመራ አዲስ መሪ ጄነራል ተስፋየ ገ/ኪዳን ሲሾሙ: የኢህአዴግ ሰራዊት ሲጠጋ የዩኑቨርስቲ ተማሪዎች ሁሉ አዲስ-አበባን ለመከላከል ወደ ስልጠና ሲወርዱና ስልጣናቸው ሳይጨርሱ ኢህአዴግ አዲስ አበባን ሲቆጠጠርና እነሱ ወደ ኬንያ ሲፈረጥጡ የነበረው ትእይንት ሁሉ አሁንም አለ::

ታዲያ የመጨረሻው ምእራፍ መጀመሪያ መሆኑን በምን እንለካው ቢባል:

  1. ሽንፈት ላለመቀበል አሁንም ህዝቡን ማታለልና እንደ ዱቄት በኗል ያሉት ህዝብ መልሰው የውስጥና የውጭ ሃይሎች ወረውናል በሚሉ ቃላት እያሽሞነሞኑ ማስታወስ ለተሳነው ህዝብ (short memory) መልሰው አለን አልተማረክንም ፎቶሾፕ ነው እያሉ ይነግሩታል ህዝቡን ጭብጨባው አልነሳቸውም :ለትግራይ ህዝብና ወዳጆች ግን በሬሳ ሳጥን ተጋድሞ እንደሞፈክር መሆኑ በሚገባ ይረዱታል:: አብይና አጃቢዎች እጣ ፈንታ እየታወቀ መፍትሄ ከመፈለግ ይልቅ አብሮ ለመጥፋት መወሰን ነው::ሁሉም መሪዎች ተሽንፈናል ከማለት “አዲስ አበባን” ለመከላከል ሲባል ከመከላከያ ጎን ቁሙ ብለው የኦሮሞ ሰንጋዎች ከወደ ጎንደር አደርሷል::
  2. የትግራይ ህዝብ ሰራዊታችን ወግተዋል የሚለው የአብይና የአማራ ክልል መሪ ሌላኛው የክተት አዋጅ ነው:: የዚህ አዋጅ እንድምታ ህዝቡ በኢትዮጵያ ውስጥ ለሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች እንዲያጠቃ የሚያነሳሳ የዘር ማጥፋቱ ምእራፍ ማገባደጃ መሆኑ ነው:: በትግራይ በመሬትና በስማይ ደብድበው የገደሉትና ያቆሰሉት ሳይበቃቸው ሁሉም ነገር ዘግተው ህዝቡ እንዳለ በረሃብ እንዲያልቅ ያደረጉት ጥረት ሁሉ በጀግናው የትግራይ ሃይል እየከሸፈ መሆኑን ሲያውቁ : በኢትዮጵያ የቀረውን የትግራይ ተወላጅ በየቀኑ በአፈሳ እያሰሩና ወደ ማይታወቁ ቦታዎች እያፈኑ ለመበቀል የሚደረግ ሙከራ ነው:: ይህ አደገኛ አካሄድ ህዝቡ ካላስቆመው እዳው ከባድ ነው::
  3. በአገር ውስጥና በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ቆይቶም ቢሆ አንዳንድ የሚያበረታቱ አስተያየቶችና መግለጫዎች ማውጣት ጀምሯል:: ነገር ግን ቆይተውም ቢሆን አገርና ህዝብ የሚታደጉ እውነታዎችን ያነገቡ አይደሉም::በትግራይ ላይ የደረሰውን በደልና ግፍ በተራ ሽምግልና የሚፈታ የእርስበርስ ግጭት አይደለም:: የተቀነባበረ አለም-አቀፍ ዘምቻ ነው: የሚቀርቡት የመፍትሄ ሃሳቦች ለደረሰው ችግር የሚመጥኑ አይደሉም:: በቅርቡ concerned citizens በሚል የተሰጠው የግልግል ሃሳብ ብዙውን የትግራይ ህዝብ አስቆጥቷል: ቢያንስ ቢያንስ የአማራ ተስፋፊ ሃይል ተሳስቷል ብሎ አይቀበልም: ሁሉም ገዳይና ሟች እኩል በማስቀመጥ ዳርዳሩን ብቻ በማር በመቀባት መርዙን ለመደበቅ የሞከረ መግለጫ ነበር:: እንደነዚህ አይነት ሙከራዎች አብይን በስልጣን ለማቆየት ከመመኮር የዘለለ ለመሰረታዊ ችግር መፍትሄ የሚያመጡ አይደሉምና ወቅቱን የጠበቀ ሌላ ተከታታይ መግለጫ እንጠብቃለን::
  4. የአለም አቀፍ ህብረተሰብ አብይ በስልጣን ለማቆየት የ8 ወራት ከንቱ ጥረት ሲያደርድ ቆይቷል:: አብይንም ማቆየት አልቻለም የትግራይ ህዝብም በጊዜው እርዳታ አልደረሰለትም:: ሁለት ስህተት ነው የተፈፀመው የትግራይ ህዝብም ሁለቴ ነው የተጎዳው:: አሁንም የትግራይ ህዝብና ሰራዊት ተገዶ የጠላትን እግር ተከትሎ በሚሰነዝረው የማጥቃት እርምጃ የተለያዩ ስሜቶች እየተፈጠሩ ነው: ሁላችንም ለአለም ህብረተሰብ አስቸኳይ መልእክታችን ማድረስ ይኖርብናል : አለማችን ካለፉት 8 ወራት የአብይና ኢሳያስ የዘር ማጥፋት ወንጀል ተግባር መማር የሚችለው አሁን በመጨረሻው ምእራፍ የተሸነፈው የአብይ ቡድን ቶሎ ቦታውን ለቆ ለፍርድ እንዲቀርብ በመተባበርና በሰላማዊ የትግራይ ተወላጆች ላይ እያደረሰ ያለውን ጥቃት እንዲቆም በመከላከል ነው::

በመጨረሻም ተወደደም ተጠላም የትግራይ ሃይል የአከባቢው ወሳኝ ኃይል ወደ መሆን ተሸጋግሯል:: “የማይቀርልህ እንግዳ አጥበቀህ ሳም” በትግርኛ “ዘይቐርየካያ ጋሻስ አጥቢቕካ ሰዓሞ” እንደሚባለው ለማይቀረው እንግዳ በሰላም ተቀብሎ ከማስተናገድና በቀጣዩ የኢትዮጵያ ጉዳይ ተወያይቶ ከመፍታት ወጪ መንፈራገጥ ከመላላጥና ጥፋት ከመጨመር ሌላ ለውጥ አያመጣም:: የሰው ልጅ ትልቁ ችሎታ ወድቆ መነሳት መቻልና ከስህተት መማር ነው:: የኢትዮጵያ ህዝብ በ30 አመታት ሰላምና እድገት ወይም በ3 አመታት የሲኦል ጊዜ ካልተማረ: ያለው አማራጭ ኢትዮጵያዊ አለመሆን ነው:: የትግራይ ህዝብ እንኳ ትግራይ መሆን የሚመርጥ ይመስለኛል::