በአስር ውሸቶች የታጀበ የኢትዮጵያ መከላከያ ሚኒስቴር መግለጫ!

ሐሙስ ምሽት የወጣው እና በሁሉም የመንግስት ሚዲያዎች እየተሰራጨ ያለውን የሚኒስቴር መስሪያቤቱ መግለጫ አስር መሰረታዊ ውሾቶችን የያዘ ነው።


1ኛ- ”ህወሓት የጀመረውን ማጥቃት፣ በማያዳግም ሁኔታ እየደመሰስነው ነው” ይላል። እውነታው ግን የኢትዮጵያ ሰራዊት ባለፈው ሳምንት ሓሙስ ከሰዓት በኋላ ሁሉም አቀፍ የማጥቃት ዘመቻ በትግራይ ሰራዊት ላይ መክፈቱ ነው። በጦር ጀት፣ በድሮን፣ በከባድ መሳሪያዎች፣ እና ብዛት ባለው እግረኛ ሰራዊት ማጥቃት መጀመሩን የሚታወቅ ነው። የአማራ ክልል የኮሙኒኬሽን ሓላፊና ሌሎች የፌደራል ሃላፊዎችም ”በማኛውም ሰዓት ጥቃት ስለምንከፍት 24 ሰዓት ዝግጁ እንድትሆኑ” ብለዉ ለተከታዮቻቸው ማሳሰቢያ ሰጥተው እንደነበር ይታወቃል። እናም ጥቃቱ የጀመሩት ራሳቸው ሆኖ ሳለ-የትግራይ ሰራዊት ጥቃት ከፈተብን የሚለው ውሸት ነው።


2ኛ- ”ህወሓት ሰሜን እዝ ላይ ጥቃት (ጭፍጨፋ) ከፈጸመ በኋላ ጦርነት እንደተጀመረ . . . ” በማለት የሰለቸ ውሸት ይደረድራል። ትግራይ በአራት አቅጣጫ ከብቦ ለማጥቃት እቅድ ወጥቶ፣ ጥቃት ሲጀመር የመከላከል እርምጃ ተወሰደ እንጂ በትግራይ መንግስት የተጀመረ ጦርነት እንዳልነበረ ይታወቃል። ”ክልሎችን ካላፈረስኩ” በሚል ጀብደኝነት የተጀመረ ጦርነት መሆኑን የሚታወቅ ነው።


ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለትግራይ ብልፅግና ኣባላት ጦርነት ከመጀመሩ አንድ ሳምንት በፊት -በሳምንት ውስጥ ጦርነት ውስጥ እንደሚገቡና -ትግራይ ያለውን አስተዳደር ማፍረስ እንደሚፈልግ ነግሯቸው ነበር- የግዚያዊ አስተዳደር ፅ/ቤት ሓላፊው ገብረመስቀል ካሳ እንደመሰከረው።


3ኛ- ”መንግስት ለ8 ወራት የመረጋጋት እና መልሶ የመገንባት ስራ እየሰራ ነበር” ይላል-ሌላው የመግለጫው ውሸት። ይህንን ማብራሪያም ኣይስፈልገውም-ጠቅላይ ሚኒስትር ነኝ ባዩ በአንደበቱ ”መቐለን በሻሻ አድርገናታል-ካሁን በኋላ ትርጉም የሌለው ክልል ነው” ብሎ መስክሮ ነበር። ከኤርትራ ሰራዊት ጋር ተባብሮ ሲያወድም፣ እንጂ መልሶ ሲገነባ አልነበረም።


4ኛ- ”ሰብኣዊ ቀውስ እንዳይባባስ፣ ቀጣይ ዓመት የምርት እጥረት እንዳይከሰት ከትግራይ ለቀን ወጥተናል” ይላል። ሲጀመር ከትግራይ ለቀው አልወጡም፣ -አሁንም ምዕራብ ትግራይን ወርረው እንደያዙ ነው ያሉት። ስለዚህ ፌደራል መንግስት ነኝ ባዩ አካል፣ ”የትግራይን መሬት የአማራ አድርገነዋል” ብሎ እየመሰከረ እንጂ ከትግራይ አልወጣም። ሲቀጥል፣ ከሌላው የትግራይ ቦታ ለትግራይ ህዝብ አስቦ የወጣ የመንግስት ሰራዊት የለም። ሙሉ በሙሉ ተሽንፎ የወጣ ሰራዊት ነው። ከ10 ሺ በላይ ምሩከኛ የሆነበት፣ አሁን የትግራይ ሰራዊት የታጠቀው መሳሪያ ያኔ በምርኮ የተገኘ ነው።


5ኛ- ”የደመሰስነው ህወሓት ከያለበት እየተሰባሰበ እያጠቃን ነው” ሲልም ይከሳል። ግፍ መሮት፣” ከማለቅ መታገል ይሻላል” ብሎ ንቅል ብሎ ወደ ትጥቅ ትግል የተቀላቀለው የትግራይ ህዝብ በተለይ ደግሞ ወጣቱ ነው። ህወሓትም እንደ አንድ የትግራይ ህዝብ አካል፣ አማራጭ ስለሌለው እየተሳተፈ ይገኛል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአንደበቱ ”የትግራይ ህዝብ ደጀን ሊሆነን አልቻለም እየወጋን ነው” ብሎ እንደመሰከረው ለህልውናው እየታገለ ያለው ምልኣተ ህዝቡ ነው። ስለዚህ ከአንድ ”የፖለቲካ ድርጅት ነን የገጠምነው” የሚለው ቧልት እና ፍጹም ውሸት ነው። መሬቱ የተቀማው፣ የግዛት አንድነቱን የተሸረፈበት፣ ራሱን በራሱ እንዳያስተዳድርና እንዳይወስን የተወሰነበት፣ በጅምላ የተጨፈጨፈው፣ ሴቶችና ህፃናቱ የተደፈሩበት ህዝብ ነው ወደ ትግል የወጣው። ስለዚህ ጦርነቱ ህዝባዊ ነው።


6ኛ- ”ወደ ሱዳን ኮሪደር ለመክፈት ሲል ወልቃይትን አጠቃ፣ . . . ወዘተ የሚል ተደጋጋሚ ክስ ተጠቅሷል። ይህ ነገር አፍ ያለው የአማራ ፖለቲከኛ ሁሉ የሚለውም ነው። ምዕራብ ትግራይ የትግራይ መሬት እንጂ የማንም አይደለም። ስለዚህ መሬቱ ኣስመልሶ ኮሪደር ማስከፈት የህልዉና ጉዳይ እንጂ ሌላ ትርጉም የለውም።


7ኛ- ”በሁለት ሳምንት አዲስ ኣበባ ለመግባት አቅደው . . .” ይላል። በሁለት ሳምንት አዲስ ኣበባ እንገባለን ያለ የትግራይ አመራር የለም። ጆኖሳይድ የፈጸሙብንን ያሉበት ድረስ እንዋጋቸዋለን ነበር የተባለው።


8ኛ- ”ጀነራል ፃድቃን በሁለት ሳምንት አዲስ ኣበባ እንገባለን አለ” -ሲልም ይጨምራል። ጀነራሉ ለኒውዮርክ ታይምስ ያለውን ያነበበ ሰው እንደዛ የሚል እቅድ አያገኝም። ጦርነት እየተካሄደበት ባለ ቦታ ጦርነቱን ለመቋጨት ግፋ ቢል ሳምንታት ይወስዳል ነበር ያለው። የማጥቃት ዘመቻው የጀመረው መንግስት ሆኖ ከሰኞ ወዲህ ደግሞ በከፍተኛ የእግረኛ ወታደር ብዛት እያጠቃ እንደሆነ ገልፆ፣ ግን ብዙም የማይሳካለቸው መሆኑን ነበር ያብራራው። አዲስ ኣበባ የሚለው ጭሆት መነሻው ምን እንደሆነ ግልፅ ነው።


9ኛ- ”ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል ከሦስት ቀን በፊት የሌ/ጀ ጻድቃንን መግለጫ በማጠናከር “…ኢትዮጵያውያንን እንደ አባቶቻቸው በመቅበር ሰላማችንን እናረጋግጣለን…” ። ይህ ፍጹም የተፈበረከት ውሸት ነው። አንድም ቀን ኢትዮጵያን እናፈርሳለን የሚል ከትግራይ መሪዎች ተስምቶ አይታወቅም። ጀነራል ፃድቃንም ሆነ ደብረፅዮን ”ኢትዮጵያውያንን እንደአባቶቻቸው እንቀብራቸዋለን” ብለው አያውቁም። ውሸት የማይሰለቸው መንግስት ግን በጥቅስ ውስጥ አስገብቶ ”አሉ” እያለ ሰርክ ይዋሻል። ጨቋኞችና ወራሪዎችን ግን እንቀብራቸዋለን፣ እንፋለማቸዋለን ሲባል ተሰምተዋል፣ ያም ትክክል ነው። ”ኢትዮጵያን ሊያፈርሱ . . . የሚለውን ተረት -ተከታይ የማደንዘዝ ውሸት ነው። ኢትዮጵያ እየፈረሰች ያለችው በአብይ አሕመድና በአማራ ሊሂቃን ነው። በወረራ እና ጭቆና ውስጥ መኖር የሚፈልግ ህዝብ ደግሞ የለም።


10ኛ- ”መከላከያ ሰራዊቱ የኢትዮጵያ ህልውናና ደህንነት እያከበረ ይገኛል”-ይላል። ውሸት! የኢትጵያውያን ደህንነት አደጋ ላይ ጥለህ፣ ጆኖሳይድ አውጀህ፣ የግኡዝ ነገር (ኢትዮጵያ) ደህንነት እንዴት ሊጠበቅ ይችላል? ይህ ሀገር አደጋ ላይ የጣለው የአማራ የማይጠረጋ ፍላጎትና መሬትን ወርሮ የመያዝ ባህሪ ነው። አብይ ደግሞ ይህንን አስፈፃሚ ፋሽሽት ነው። በዚህ ሂደት የህልውና አደጋ የተጋረጠበት የትግራይ ህዝብ እንጂ ሌላ ኣይደለም።