ጋዜጠኛው እስካሁን እንደጠፋ ነው!

ኢትዮ-ፎረም የጋዜጠኝነት ሙያ በስርዓቱ ለመተግበር ሲጥር የነበረ ሚዲያ ነው። ጥልቀት ያለው ትንታኔ በማቅረብም ይታወቅ ነበር። ከዚህ የበይነ-መረብ ሚዲያ ጀርባ የነበሩት ጋዜጠኞች ደግሞ በዋናነት ያየሰው ሽመልስ እና አበባ ባዩ ናቸው። ጋዜጠኛ ያየሰው ሽመልስ ይዘት ያዘጋጃል፣ አበበ ባዩ ደግሞ ዜና ከማጠናቀር በተጨማሪ በጆሮ ገብ ድምፁ የጣብያዉ ይዞቶች ያነብ ነበር።

ሁለቱም ጋዜጠኞች በኢትዮጵያ መንግስት በተደጋጋሚ የታሰሩና ኣካላዊ ድብደባም የደረሰባቸው ናቸው። ያየሰው ሽመልስ በወገብ መታመም የሚሰቃይ ሲሆን፣ አበበ ባዩ ደግሞ በአንድ ወቅት የፀጥታ ሃይሎች ኩፉኛ ደብድበዉት የሞተ መስሏቸው ከፍሳሽ መተላለፍያ ቦታ ጥለውት መሄዳቻው ይታወሳል። ከዚህ ጋር የተያያዘ የጤና እክል አለበት።

ሁለቱም ጋዜጠኞች በ2013 ዓ/ም ከአውሎ ሚዲያ ሰራተኞች እና ሌሎች ጋዜጠኛች ለ49 ቀናት በአዋሽ ዓርባ ታስረው የተፈቱ ሲሆን፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ ስርዓቱ ግንቦት ወር ላይ ብዙ ጋዜጠኞች ሲያስር የታሰሩ ናቸው።

ነገር ግን ጋዜጠኛ ያየሰው ሽመልስ ፍርድ ቤት በ10 ሺህ ብር ዋስ ለቆት የነበረ ቢሆንም፣ ፖሊስ ሰኔ 21 ፣ 2014 ዓ/ም እንደገና አስሮታል። እስካ አሁንም የት እንዳለ አልታወቀም።

ያየሰው ከሁለት ዓመት በፊት መጋቢት 2012 ዓ/ም “መንግሥት በኮሮና ቫይረስ ምክንያት 200 ሺሕ ጉድጓዶች እንዲዘጋጁ አዝዟል” የሚል ዘገባ አሰራጭቷል በሚል ታስሮ ብዙ ጊዜ በእስር እንዳሳለፈ ይታወቃል። አሁን ለአራተኛ ጊዜ መታሰሩ ነው።

በተመሳሳይ አበበ ባዩም ENN በአብይ መንግስት ከተዘጋ በኋላ በBBC Action ተቀጥሮ ብዙ ሳይቆይ በስርዓቱ ታስሮ ከአንድ ዓመት በላይ ጊዜ ሂወቱን በማረሚያ ቤት አሳልፏል። በ2013 ዓ/ም ወደ ሁለት ወር የሚጠጋ ጊዜ አዋሽ አርባ ታስሮ ቆይቷል። አሁን ለሶስተኛ ጊዜ በሰኔ 21 የታሰረ ሲሆን በአዋሽ አራባ እንደሚገኝ ከስፍራው የተለቀቁ ታሳሪዎችን እማኝ አድርገው ቤተሰቡ ለአዲስ ስታንዳርድ ገልፀዋል።

%d bloggers like this: