በወቅታዊ ጉዳዮች መግለጫ የሰጡት የትግራይ ሰራዊት ዋና ኣዛዥ ጀነራል ታደሰ ወረደ እንደገለፁት፣ ሰሞኑን በኢትዮጵያ መንግስት የተሰነዘረው መጠነ ሰፊ ማጥቃት፣ የነበረውን የተናጠል ተኩስ ኣቁም ስምምነት የጣሰ እና የሰላም እድል የዘጋ መሆኑን አብራርተዋል። ጀነራሉ ”የትግራይ ሰራዊት ጥቃት በተከፈተብን ሁሉም ግንባሮች በብቃት እየተፋለመ ነው” ብለዋል።
ስርዓቱ ህዝባችንን ረሃብ እንደ ጦር ማሳሪያ በመጠቀም እየፈጀ እና ሁሉም ዓይነት ኣገልግሎቶች ዘግቶ ለመጨረስ የሚደረገውን ግፍ እንዳይበቃው፣ ”ተብዳክሟል” በሚል ስሌት እንደገና ሌላ ዙር ወረራ ሲፈፀምብን ዝም ብለን ልናይ ኣንችልም ያሉት ጀነራል ታደሰ ወረደ፣ ያጠቃንን ሃይል በበቂ ጸረ-ማጥቃት ስራ፣ ስትራቴጂያዊ ከሚባሉ የውጊያ ቦታዎች አስለቅቀን እየበተንነው ነው” ብለዋል።
ጉዳያችን ሰላም ስለሆነ ይህን ያህል ሰው ገደልን፣ ያን ያህል ማረክን ብለን መናገር አንፈልግም ያሉት ጀኔራሉ፣ እስከ ኣምስት ሺ የሚጠጋ ወታደር እንደተማረከ እና በተለይ ደግሞ እስካሁን ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ብዛት ያላቸው የኮማንዶዎችና የሪፓብሊካን ጋርድ ኣባላትን እንደተማረኩ ግን ሳይገልፁ ኣላለፉም።
ያበለ ሚዲያ
25 ነሓሴ 2014 ዓ/ም