ትግራይና አማራ

ትግራይና አማራ: በአንድ ሀገር የምንኖር የሁለት ዓለም ህዝቦች!

ዛሬ በኢቢኤስ ቴሌቪዥን የዜና እወጃ ላይ አንድ ዳሰሳ ስመለከት ነበር፡፡ ሰላም ፣ ፍቅርና መትረፍረፍ ለኢትዮጵያ የሚል እንቅስቃሴ ሊጀመር ነው ይላል፡፡ የእንቅስቃሴው መሪ ቃል ደግሞ ፈገግ በይ ሀገሬ የሚል ነው፡፡ ይታያችሁ እንግዲህ ፣ ፈገግ በይ ሀገሬ የሚለው እንቅስቃሴ እየተደረገ ያለው የሀገሪቱ አንድ አካል የሆነው ትግራይ የዘር ማጥፋት ዘመቻ ታውጆበት 24 ሰዓት በደምና በእንባ በሚታጠብበት፣ በህፃናት ላይ ከሰማይና ከምድር ቦንብና መርዛማ ኬሚካል በሚዘንብበት፣ ራሱን እንደ ኢትዮጵያዊ ቆጥሮ ለሶስት ሺህ አመታት የዚህች መተተኛ ሀገር ዜጋ ሆኖ በኖረ የራስ ህዝብ ላይ የጎረቤት ሀገር ሰራዊት አስገብቶ መጠነ ሰፊ ጭፍጨፋ በሚደረግበት፣ የማያባራ ሞትና መደፈር በሰፈነበት፣ በመላዋ ትግራይ ስፍር ቁጥር የሌለው መከራ በሚደርስበት ሰዓት ነው፡፡

እንዲህ ዓይነቱን ሀሳብ የሚያመነጩት፣ የሚያስተጋቡትና የሚከተሉት አካላት እነዛ በትግራይ ሰቆቃ የደስታ ሲቃ የሚተናነቃቸው፣ የሐሴት እንባ የሚያጥባቸው፣ ለዘመናት የተመኙትና የተገበሩት የጥፋት ዘመቻ እውን ሆኖ በማየታቸው ሌተቀን ምስጋናቸውን የሚገልፁ የአማራ ልሂቃንና ተከታዮቻቸው ናቸው፡፡ የዘመናት ባላንጣችን የሆነው የትግራይ ህዝብ በጥይት፣ በረሀብ በውሀ ጥም፣ በበሽታና በመርዛማ ኬሚካል እያለቀልሽ ነው ፈገግ በይ ኢትዮጵያዬ፣ ይህን ህዝብ ከምድረ-ገፅ ለማጥፋት ያቀድነው የቀየስነውና የተገበርነው አካሔድ ፍሬ አፍርቷልና የተትረፈረፈ ሰላምና ፍቅር ታገኝያለሽ ፈገግ በይ ሀገሬ እያሉ ያሉት የዘወትር ምኞታቸውና ህልማቸው ይኸው የሆነው የአማራ ልሂቃንና ተከታዮቻቸው ናቸው፡፡

እንዲህ እያሉ ያሉት እነዛ የኢትዮጵያ፣ የኤርትራ፣ የሶማሊያ ሰራዊቶችን፣ የአረብ ድሮኖችን፣ የአማራ ሐይሎችን (ልዩ ሀይል፣ ፖሊስ፣ ሚሊሻ፣ ፋኖ)፣ ከዘጠኙም ክልሎች የተውጣጡ ልዩ ሐይሎችንና የተለያዩ ሀገራት ወታደራዊ አማካሪዎችን በአንድ ጊዜ በትግራይ ላይ አሰማርተው የሀገሪቱን 5 ከመቶ የሆነውን የትግራይን ህዝብ በአንድ ወር ውስጥ ለመፍጀት አቅደው የተገበሩ የአማራ ልሂቃንና ተከታዮቻቸው ናቸው፡፡

እንዲህ እያሉ ያሉት ያንን በቂምበቀል የሰከረውን ኢሳያስን የዘመናት በቀሉን እንዲወጣ ደመወዝ እየከፈሉና ትጥቅና ስንቅ እያቀረቡ፣ ለሰላሳ አመታት ያህል ያሰለጠንካቸውን ክፍለጦሮች ሁሉ አስገብተህ በትግራይ ላይ ምድራዊ ግፍ ሁሉ ፈፅም ብለው የትግራይን ህዝብ ያስፈጁት፣ ከስድስት አመት ህፃናት ጀምሮ ሴቶችን ያስደፈሩት፣ የትግራይን ኢኮኖሚያዊ ሀይማኖታዊ ባህላዊ ታሪካዊ ሀብት ሁሉ እንዲወድም ያደረጉት፣ ከጥይት የተረፈውን ህዝብ በረሀብ እንዲያልቅ የፈረዱት፣ ከሀገርና ህዝብ በላይ የትግራይ ጥላቻ ያየለባቸው የአማራ ልሂቃንና ተከታዮቻቸው ናቸው፡፡እንዲህ እያሉ ያሉት እነዛ ለክርስቶስ ካላቸው ፍቅር ይልቅ ለትግራይ ህዝብ ያላቸው ጥላቻ ይበልጥባቸዋል የተባለላቸው፣ እነዛ ለስድስት ወራት ያህል የኤርትራ ሰራዊት አልገባም ብለው የክህደትና የውሸት መረጃ እያስተጋቡ ዓለምን ሲያወናብዱ የነበሩት፣ እነዛ ሀገራችን እኮ ለሌሎችም የሚተርፍ ሰራዊት ያላት ነች እያሉ ፈጣሪ በሌለባቸው አብያተ ክርስቲያን ሲምሉ የነበሩት፣ እነዛ በትግራይ ህዝብ መጨፍጨፍ መደፈርና ማለቅ ሲሳለቁ ሲደሰቱ የነበሩት የአማራ ልሂቃን ናቸው፡፡ኢትዮጵያ ማለት ድርና ማጓ፣ መንፈስና ስጋዋ፣ ባህሏና ድባቧ በነዚህ ነውረኞች የተገነባች ነች፡፡ ኢትዮጵያውያን ማለት በይዘትም በመልክም እነሱ ማለት ናቸው፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ ማለት የነሱን ባህል፣ ቋንቋ ፣ ስነልቦና፣ አስተሳሰብ፣ ማንነት ተላብሶ ራሱን ክዶና አዋርዶ የሚኖረው ህዝብ ማለት ነው፡፡

አሁን ሳስበው በዚህች ሀገር ውስጥ የትግራይ ህዝብና የኢትዮጵያ ህዝብ በአንድ ሀገር የሚኖር የሁለት አለም ፍጡር ኖሯል፡፡ የትግራይ ህዝብ እንደምን ኢትዮጵያ የኔ ነች ብሎ አመነ፡፡ እንዴት ለብዙ አመታት ለህልውናዋ እየደከመ፣ ለሉአላዊነቷ እየደማ፣ ለእድገትዋ እየጣረ፣ ራሱን እየጎዳ እሷን እየገነባ ኖረ፡፡ ይህ ህዝብ እንዴት እነዚህን ምድራዊ ደመኞቹ እሱን ካላጠፉ መቼም እንደማይተኙ መንቃት ተሳነው፣ ይህ ህዝብ እንዴት እሳት ሲተኛ ገለባ ይጎበኘዋል እንደሚባለው እሱ አንቀላፍቶ እነሱ የጎበኙት እለት መረን በለቀቀ ጭካኔያቸው እንደሚያጠፉት ዘንግቶ ለዚህ የመከራ ዘመን ደረሰ…..፡፡

ጥያቄው ማለቂያ የለውም፡፡ የትግራይ ህዝብ ከማይመስለው የኢትዮጵያ ህዝብ ጋር የአንድ ሀገር ዜጋ ሆኖ ለመኖር የመወሰኑ ስህተት ለዚህ እልቂት አብቅቶታል፡፡ በእሱ እልቂት በኢትዮጵያ ምድር ሰላምና ፍቅር ተትረፍርፏል፡፡ በእሱ እልቂት በኢትዮጵያ ምድር ፈገግታ ተዘርቷል፡፡ የትግራይ ህዝብ እልቂት በዳንኤል ክብረት አንደበት የኢትዮጵያ ህዝብ መንግስትና መከላከያ ተናብበው ያመጡት ስኬታማ ውጤት ነው፡፡ የትግራይ ህዝብ እልቂት በሀይሌ ገብረስላሴ አንደበት የአብይ አህመድ ብልጠት የተሞላበት የጦርነት አመራር ውጤት ነው፡፡ ኢትዮጵያ ሆይ ! በኛ ሞት ፈገግ ያልሽውን ያህል በእኛ ትንሳኤ የምታለቅሺበት ቀን እሩቅ አይሆንም፡፡

ድል ለትግራይ ህዝብ !