የጠቅላይ ሚኒስትር ኣብይ ኣሕመድ ያልተቋረጠ ውሸት እና የመንግስት ሚድያዎች ‘የገደል ማሚቶ’ ሚና ብጥልቀት ሲፈተሽ።

ሰለ ቀድሞው የ ኣሜሪካ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ወቀሳዊ ሓሳብ የሚያነሱ ሰዎች “ውሸታም” ናቸው ይሏቸዋል። የተወሰኑትም የቀድሞውን ፕሬዝደንት በበሽታ ደረጃ የሚዋሹ (pathological liar) ናቸው ሲሉ በድፍረት ተናግረዋል።

የጋናው ምክትል ፕሬዝደንት ማሃሙዱ ባውምያ ም በብዙዎች ዘንድ የጋና ትልቁ ውሸታም የሚል ስም ተስጥቷቸዋል።

ወደ ኢትዮጵያ ስንመለስ ጠቅላይ ሚኒስተር ኣብይ ኣሕመድ ወደ ስልጣን ከመጡ ግዜ ጀምሮ ብዙ ውሸቶችን እንደተናገሩ ከሚሰጥዋቸው መግለጫዎች መረዳት ይቻላል። ነገር ግን ኣሁን ኣሳሳቢ ስለሆነው ጉዳይ ምክንያት በማድረግ ከጦርነቱ ቡኋላ የሰጥዋቸውን የተምታቱ መገለጫዎች እና ውሸቶች እንመልከት።

ጥቅምት መጨረሻ ላይ ትግራይ ለይ የታወጀው ጦርነት ይፋ ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስተር ኣብይ ኣሀመድ ከጦርነቱ ቡኋላ የዋሹት የመጀመርያው ውሸት “ሰሜን እዝ ስለተጠቃ ህግ የማስከበር ዘመቻውን በይፋ ጀምረናል።” የሚል ነው። እዚጋ ሁለት ውሸቶች ናቸው ያሉት። የመጀመርያው ሰሜን እዝ በትግራይ ሃይሎች ኣለመጠቃቱ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ የተደረገው ህግ የማስከበር ዘመቻ ሳይሆን ጦርነት መሆኑ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጦርነት ነው ብለው ማመን ኣልፈለጉም “ልክ ወለጋ ላይ ሶማልያ ላይ እንዳደረግነው ነው” ሲሉ ኣቃለሉት። ሚድያዎች መንግስት ያለውን ሁሉ ሳይጠይቁ የሚያስተላልፉ ቱቦዎች ሆኑ። ሁሉም ተመሳሳይ ዜና ነው የሚቀባበሉት።

በመቀጠልም “የኢትዮጵያ ሰራዊት መቐለ ሲገባ በኣንዲት ከተማ የኣንድም ሰው ሂወት ሳይጠፋ ነው።” በማለት የብዙዎችን ሞት፥ መቁሰልና መፈናቀል ካዱ። ከጥቂት ግዚያት ቡኋላ ደግሞ “ውግያ ጥፋት ነው። በትግራይ ክልልም የደረሱ ጥፋቶች ኣሉ።” ሲሉ ሰራዊቱ ህዝቡ ላይ ጥፋት እንዳደረሰ ኣመኑ።

የኤርትራ ሰራዊት ወደ ትግራይ ስለመግባቱ በሚመለከት ጉዳይ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ እስከ ስርኣቱን ደግፈው የሚፅፉ ኣክቲቪስቶች ሽምጥጥ ኣድርገው ካዱ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ” ራቁታቸውን የሄዱ ሰዎች የኤርትራ ሰራዊት ልብስ ለብሰው ተመልሰዋል። ለዚህ ነው ኤርትራ ወጋን የሚሉት” ፣”ህወሓቶች በኣልመዳ ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ የኤርትራ ሰራዊት ልብስ እያመረተች ነው” በማለት በተደጋጋሚ ሲዋሹ ነበር። የኤርትራ ሰራዊት መግባት ይፋ ሲሆን የስርኣቱ ደጋፊዎች “መንግስት ለምን ሲዋሸን ነበር” ብለው ኣልጠየቁም። በተመሳሳይ የሶማልያ ወታደሮች በጦርነቱ ስለመሳተፋቸው መንግስት “በጭራሽ” ሲል ነው የመለሰው። የሶማልያ እናቶች ግን ኣደባባይ ወጥተው ወደ ኤርትራ ለስልጠና ልካችሁ የት እንደደረሱ ማወቅ ያልቻልን እናቶች ምላሽ እንፈልጋለን ሲሉ ኣደባባይ ወጡ። ቀጥሎም የሶማልያ ብሄራዊ ደህንነት ኣማካሪ ዓብዲ ሳዒድ 5,000 ወታደሮች ለስልጠና ወደ ኤርትራ ተልከው እንደነበር ከስምንት ወራት በኋላ አምነዋል።

የተባበሩት መንግስታት ሰብኣዊ መብት ኮሚሽን ደግሞ እነዚህ ወታደሮች ከኤርትራ ወደ ትግራይ ተጓጉዘው ጦርነት ውስጥ እንደተሳተፉ እና ኣክሱም ከተማ ላይ በነበረው የንፁሃን ዜጎች ጭፍጨፋ እጃቸው እንዳለበት በሪፖርቱ አካትቶ እንደነበር ይታወሳል። በዚህ ጉዳይም በተመሳሳይ የጠየቀ ኣካል እምብዛም ነው።

“በየትኛውም ኣለም ታይቶ በማይታወቅ መልኩ በ ሶስት ሳምንት ውስጥ ኣለቀ የተባለው ጦርነት 9 ወራት ሲያስቆጥር ጠንከር ያሉ ጥያቄዎችን የሚያቀርብ ጋዜጠኛ በጣት የሚቆጠር ነው።

ወታደራዊ መሪውም ” ጦርነቱ ኮ ኣልቋል። የምንዋጋው ብርጌድ እና ክፍለ ጦር የለም። ኣሁን እኛ እየፈለግን ያለነው ደብረፅዮን የት ነው? ጌታቸው የት ነው?” ብለን እየፈለግን ነው ሲሉ ጦርነቱ ማለቁን በእርግጠኝነት ተናገሩ። “የነበራቸውን መሳርያ ራዳር፣ ምሳኤልና ሮኬቶች ኣሁን የለም። ኣንድ ክላሽ ለ ኣምስት ሰው ነው የሚጠቀሙት።” ሲሉ የትግራይ ሰራዊት ሙሉ በሙሉ በሚባል መልኩ መደምሰሱ ተናገሩ። ሚድያዎቹም ይህንኑ ሲቀባበሉት ነበር።

በጦርነቱ ምክንያት ከትግራይ ወደ ሱዳን ስለተሰደዱ የትግራይ ተወላጆች ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሲመልሱ “ከስደተኞቹ ማሃል ሴቶችና ህፃናት የሉም። ወጣቶች ብቻ ናቸው ሲሉ” ተናገሩ። የተለያዩ የእርዳታ ድርጅቶችና የዓለም ሚድያዎች ግን ከነ ማስረጃው ከኣጠቃላይ ስደተኛ 33% ህፃናት እንደሆኑ ሴቶችና እናቶችም በብዛት ወደ ሱዳን እንደተሰደዱ ይፋ ኣደረጉ።

መንግስት በተደጋጋሚ የትግራይ ሃይሎች ተደምስሰዋል ሲል የስርኣቱ ታማኝ ደጋፊዎች ደግሞ በሺዎች የሚቆጠሩ ተከታዮች ባለበት ማህበረዊ ገፃቸው የተለያዩ የትግራይ መሪዎች ፕሬዝደንት ደብፅዮንን ጨምሮ ሞተዋል ብለው በእርግጠኝነት ሲናገሩ እና ጋዜጠኞች ተብለው ወደ ስቱድዮ የሚታደሙ ሰዎች መriዎቹ የት ቦታ እና እንዴት እንደሞቱ የትኛው ኣካላቸው የት እንደተቀበረ ሲገልፁ ከረሙ። መሪዎቹ መቐለ ገብተው የሚያሳይ ቪድዮ ሲወጣና በተደጋጋሚ ቃለ መጠየቅ ሲሰጡ ለሀሰተኛ መረጃው ይቅርታ የጠየቀ ኣካል የለም። መንግስት ውሸትን እንደፖሊሲ የተጠቀመበት ይመስላል።

የትግራይ ሃህሎች መቐለን ሲቆጣጠሩም መንግስት በተለያየ ግዜ የተለያዩ ምክንያቶችን ነው ያስቀመጠው። ወቅቱ የክረምት ስለሆነ የትግራይ ኣርሶ ኣደር እንዲያርስ ነው፣ ህዝቡ መከላከያውን እየወጋ ስለሆነ፣ የፅሞና ግዜ ለመስጠት የሚሉ ምላሾችን ሲሰጥ ነበር። “ከዚህ ቡኃላ ለኢትዮጵያ ስጋት እንደማይሆን ስላደረግነው ነው” ሲልም ሰራዊቱ ምንም ኣቅም እንድሌለው ገለፀ።

የትግራይ መከላከያ ሰራዊት “የጦርነት ወንጀለኞችን የገቡበት ገብተን ለመያዝ” በሚል ከ ትግራይ ኣልፈው የተለያዩ የ ኣማራ ክልል ከተሞችን ሲቆጣጠሩም መንግስትና መንግስታዊ ሚድያዎች “ሰርገው ገብተው ነበር ተደመሰሱ፣ ወደ መጡበት ተመለሱ፣ ተመትተው ተበታተኑ” እያሉ ህዝቡን ሲዋሹት ይታያል። ቅርብ ግዜ እንደ የ ኢትዮጵያ ብሮድካስት ኮርፖሬሽን እና ፋና የመሳሰሉትን ጨምሮ ሌሎች ሚድያዎችም የትግራይ መከለከያ ሰራዊት ኣባላት የለጠፉትን የድል ፎቶ በመውሰድ ህዝቡን በንቀት ሲዋሹት ታይተዋል።


መንግስትን ብቻ የሚሰሙ የኢትዮጵያ ሚድያዎች

የ ሩዋንዳ የዓለም ኣቀፍ ወንጀለኞች ፍርድ ቤት እንደ ኣውሮጳውያን ኣቆጣጠር በ 2003 ሩዋንዳውያኑ ጋዜጠኞች ፈርዲናንድ ናሂማናን እና ጄን ቦሶኮ በዘር ጨፍጫፋ እና ሰብኣዊነት ላይ በፈፀሙት ወንጀል በሚል ከሷዋቸዋል። በሁለቱም ጋዜጠኞች ላይ የተመሰረተው ክስ ሚድያ የዘር ጭፍጨፋ ላይ ስላለው ኣሉታዊ ኣስተዋፅኦ ብዙ ጥያቄዎች እንዲነሱ ኣድርጓል።

የ ሩዋንዳ ባህል ኣንትሮፖሎጂስት ቻርለስ ሚሮንኮ በመቶዎች ከሚቆጠሩ በ ዘር ጭፍጨፋው ከተሳተፉት ሰዎች ያገኘውን ምላሽ በማጠቃለል እና ጥናቶችን በማካሄድ ብሚድያ የሚተላለፉ የጥላቻ መልእክቶች የዘር ጭፍጨፋ እንዲካሄድ ቀጥተኛ ኣስተዋፅኦ እንዳላቸው ይገልፃል። በሚድያዎች ኣንድን ህዝብ ከሰውነት በታች ኣድርጎ በመግለፅ የሚተላለፍ የጥላቻ ንግግር ወደ እርስ በእርስ ጦርነት እና ወደ ዘር ማፅዳት ነው የሚመራው ይላል።


የኢትዮጵያ ሚድያዎች እና የሞያው የስነምግባር መርሆች

የኢትዮጵያን የመንግስት ሚድያዎች ከተወሰኑ የጋዜጠኝነት የሞያው መርሆች ጋር ስናየው የሚታረቅ ኣይደለም።

1፡ እውነትን መፈለግ

ስለ ኣንድ ጉዳይ እውነተኛ መረጃ ለመስጠት ማጣራት የመጀመርያው ስራ ይሆናል። የት፣ በማን፣ ለምን የሚሉ ጥያቄዎችና ድህረ ሁኔታዎችን ማካተት ይጠይቃል። የ ኢትዮጵያ ሚድያዎች ከዚህ ኣንፃር ከ ኣንድ ወገን የሚመጣን መረጃ ካለ ምንም ማጣራት እና ጥያቄ እንደወረደ ያቀርቡታል።

2፡ ትክክለኛነት እና ህጋዊነት

ትክክለኛ መረጃ በማስተላለፍ በኩልም የኢትዮጵያ ሚድያዎች ክፍተት ትልቅ ነው። ህግን እና የሞያ ስነምግባሩን የሚፃረሩ ያልተፈጠሩ ክስተቶችን እንደተፈጠሩ ኣድርጎ ማሳየት። ለምሳሌ ያክል በቅርቡ ከ ሳውዲ ኣረብያ የተመለሱ የትግራይ ተወለጆች፣ ኣዲስ ኣበባ ሽሮ ሜዳ የ ሃገር ልብስ ይሸጡ የነበሩ የትግራይ ተወላጅ ነጋዴዎች እና በማንነታቸው ምክንያት የታሰሩ ተጋሩን ወደ እስር በማጎር ጦርነት ላይ የተማረኩ ተብለው በ ሚድያዎች ቀርበዋል። ብዙዎች ስራ ላይ የነበሩ ሲቪል ቤተሰቦቻቸው፣ ጓደኞቻቸው እና የሚያውቁዋቸው ሰዎች ሙርከኞች ተብለው በ ሚድያ ሲታዩ ኣይተዋል።

3፡ ፍትሃዊነት እና ሚዛናዊነት

ሚድያ ህዝቡን ነው ማገልገል ያለበት። የ ኢትዮጵያ ሚድያዎች በመንግስት በኩል የሚወጡት መግለጫዎችን ብቻ መዘገብ እና ከመንግስት ትእዛዝ በመቀበል ኣንዱን ወገን ብቻ የሚያገለግሉ እና
ለሚዛናዊነት የማይጨነቁ ናቸው። መንግስት “መቐለን ለቀን የወጣነው የትግራይ ገበሬ እንዲያርስ በማሰብ ነው” ሲል የመንግስትን ምላሽ ብቻ እውነት እንደሆነ ኣድርገው ያቀርባሉ።

በትግራይ ሰራዊት የተማረኩ በሺዎች የሚቆጠሩ ሙርከኞች ጀነራል ባጫ ደበሌ ፎቶ ሾፕ ነው ስላሉ ብቻ የለበሱት ወታደራዊ ልብስ እየታየ ለማጣራት እና ለመጠየቅ የደፈረ ኣካል ኣልነበረም።

4፡ ገለልተኝነት

ሚዛናዊነት የሌለው ሚድያ ገለልተኛ ሊሆን ኣይችልም። በኣሁኑ ግዜ መንግስትን የሚወቅሱ ጋዜጦችና መፅሄቶች ማየት የተለመደ ኣይደለም። ሚድያዎቹ ኣንዱን ኣካል በማወደስ ሌላውን ደግሞ ስም በመስጠት ተጠምደዋል።

5፡ ስም ማጥፋት እና ትክክለኛ ያልሆነ ገፅታ

ኣንድን ህዝብ ኢላማ ባደረገ መልኩ “ትግርኛ ተናጋሪዎች” ተብለው ከተሰሩ ዶክመንተሪዎች ጀምሮ የትግራይ ህዝብ መከላከያን ወጋው የሚል የስም ማጥፋት ዘመቻ፤ የትግራይ ሰራዊት ሃሽሽ ይጠቀማል የሚል ከ እውነት የራቀ ኣሉባልታ እና ሌሎች ስለ ትግራይ መሪዎችም ሆነ ህዝብ የሚሰራጩ የሃሰት መረጃዎች የ ኢትዮጵያ ሚድያዎች ስም ማጥፋት እና ትክክለኛ ያልሆነ ገፅታን በ ማሳየት ሞያውን ኣቅልለውታል።

ጠቅላይ ሚኒስተር ኣብይ ኣህመድ በእሳቸው የስልጣን ዘመን ሚድያ ዘግቶ ጋዜጠኛ ኣስሮ እኔ ብቻ ጎብለል ልሁን የሚባልበት ግዜ እንዳበቃ ተናግረው የነበረ ቢሆንም የተዘጉ ሚድያዎችን መዘርዘር ይቻላል። LTV፣ ኣውሎ፣ ኢትዮ-ፎረም፣ ኢኤንኤን፣ ሁሉም የትግራይ ሚዲያዎች መጥቀስ ይቻላል። ከወራት በፊት “መረጃ እንደ ህብረተ ሰባዊ ሃብት” በሚል መሪ ቃል በተከበረው የ ኣለም የ ነፃ ፕረስ ቀን international press institute ባወጣው መረጃ ላይ በ 12 ወራት ውስጥ 49 ጋዜጠኞች የተገደሉ ሲሆን 43 ቀጥታ ከ ጋዜጠኝነት ሞያቸው ጋር በተያያዘ እንደተገደሉ ገልፅዋል።

በቅርብ ግዜ የተፈቱት የ ኢትዮ ፎረም እና የኣውሎ ሚድያ ጋዜጠኞችም በሞያቸው ምክንያት ለወራት ኣዋሽ ኣርባ ታስረው እንደነበር ይታወቃል።